በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ዘንድሮ ዕዳዋን ሳትከፍል ቀረች


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ ከተማ

ኢትዮጵያ ላለባት ዕዳ ለዓለምአቀፍ አበዳሪዎቿ ዛሬ፤ ታኅሣስ 16 ይጠበቅባት የነበረውን የወለድ ክፍያ ሳትፈፅም ቀረች።

ሃገሪቱ ባላት ብቸኛ የዓለምአቀፍ የመንግሥት ቦንድ መክፈል የነበረባት 33 ሚሊየን ዶላር ነበር።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝና ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. ፕሪቶሪያ ላይ በተፈረመ ፀብን የማቆም ስምምነት ባበቃው የሁለት ዓመት የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የበረታ የገንዘብ ችግር የደረሰባት መሆኑን በማሳወቅ የዚህ ዓመት ዕዳዋን መክፈል የማትችል መሆኑን በያዝነው የአውሮፓ ወር መጀመሪያ ላይ መጠቋቆሟን ዘገባው አስታውሷል።

በ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሽያጭ ላገኘችው ብድር ወለዱን እስካለፈው ታኅሣሥ 1 መክፈል የነበረባት ቢሆንም በተሰጣት ተጨማሪ የ14 ቀናት 'የእፎይታ ጊዜ' ውስጥም ክፍያውን መፈፀም ተስኗታል።

ካለፈው ሣምንት የመጨረሻ ቀናትና ከትናንቱ የገና ዝግ በፊት በነበረው የዓለምአቀፍ የባንክ አገልግሎት የዕፎይታ ጊዜው የመጨረሻ የሥራ ቀን፣ ያለፈው ዓርብ ነበር።

እንዲህ ከሆነ ኢትዮጵያ በተላከላት የክፍያ መፈፀሚያ ሠነድ መሠረት ዕዳዋን በወቅቱ፣ ማለትም ታኅሣስ 5 መክፈል አትችልም ማለት ነው”

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ካለፈው ዓርብ አንስቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምንም ምላሽ እንዳልሰጡት ሮይተርስ አክሎ ጠቁሟል።

በሕዝቧ ቁጥር በአህጉሩ ሁለተኛ የሆነችው ሀገር የሚጠበቅባቸውን የብድር ወለድ መክፈል ካልቻሉ የአፍሪካ አገሮች ከዛምቢያና ከጋና ጋር ሦስተኛዋ ሆናለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በቡድን ሃያ-መር መርኃግብር መሠረት የወለድ መጠንና የክፍያ ጊዜ ማስተካከያ የጠየቀችው በ2013 ዓ.ም. አጋማሽ እንደነበር ዘገባው አስታውሶ የክፍያው ሂደት መጀመሪያ ላይ የዘገየው በእርስ በርስ ጦርነት ቢሆንም የውጭ ምንዛሪ ክምችቷ በመሟጠጡና የግሽበት መጠኑ በመናሩ ቻይናን ጨምሮ የሁለት ወገን ቀጥተኛ አበዳሪዎች የክፍያ ጊዜውን ለጊዜው ለማቆም ተስማምተው ቆይተዋል።

ከጡረታ ፈንድ ተቋማትና ቦንዱን ከያዙት የግል ዘርፍ አበዳሪዎቹ ጋር ጎን ለጎን ሲያካሂዳቸው የነበሩ ድርድሮችም መክሸፋቸውን መንግሥቱ ባለፈው ኅዳር 28 አሳውቋል።

“እንዲህ ከሆነ ኢትዮጵያ በተላከላት የክፍያ መፈፀሚያ ሠነድ መሠረት ዕዳዋን በወቅቱ፣ ማለትም ታኅሣስ 5 መክፈል አትችልም ማለት ነው” ብሎ የደመደመው የብድር መታመን መጠን ደረጃዎችን ከሚሰጡ ዓለምአቀፍ ተቋማት አንዱ የሆነው ስታንዳርድ ኤንድ ፑርስ ወይም በምኅፃር ኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል የኢትዮጵያን ቦንድ “ሊከፈል የማይችል” ወደሚል ዶሴ እንደከተተው የሮይተርስ ዘገባ አክሎ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG