በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋልድባው መነኩሴ ነጻ ወጥቷል ወዳሉት ገዳም መመለሳቸውን ተናገሩ


አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም
አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም

ከትላልቆቹ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተከርስቲያን ገዳማት የዋልድባ ገዳም ተወካይ የነበሩት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያምን ዋልድባ ገዳም ነጻ በመውጣቱ ወደ ገዳሙ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

አባ ገብረየሱስ በቀደመው መንግሥት እስርና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን የገለጹልን ሲሆን፣ አካባቢው ነጻ በመውጣቱ፣ ከተባረሩበትና እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ ነበረበት የዋልድባ ገዳም ሰሞኑን የተመለሱ መሆኑንም አጫውተውናል፡፡

የዋልድባ ገዳም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከስቲያን ከአሏት ታላላቅ ገዳማት አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

አካባቢውንና የፌዴራል መንግሥቱን ይቆጣጠር ከነበረው፣ የቀደመው መንግሥት ጋር በተፈጠረ ግጭት፣ ከታሰሩና ከገዳሙ እንዲባረሩ ከተደረጉ መነኮሳት መካከል፣ መጋቢ ስርዓት አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም አንዱ ናቸው፡፡ የዋልድባ ገዳም አብረንታንት ቤተ ሚናስ ተወካይ ሆነው ለዓመታት አገልግለዋል። የገዳሙን ቦታዎች ለስኳር ፋብሪካ መታሰቡን በመቃወማቸው እንደ ፖለቲካ እስረኛ በሽብር ወንጀል ተከሰው በማዕከላዊ እስር ቤትና ኋላም በቅሊንጦ ወህኒ ቤት መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ መነኩሴው አባ ኪዳነ ማርያም፣

"የዋልድባና የህወሓት ፍጥጫ" የሚል መጽሀፍ አውጥተዋል፡፡

በመጽሀፉ ዙሪያ ወደፊት የምንምለሰበት ሆኖ፣ ለዛሬው በትግራይ እየተካሄደ ካለው የሰሞኑ ግጭት ጋር ገዳሙ ስለሚገኝበት ሁኔታ አነጋግረናቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የዋልድባው መነኩሴ ነጻ ወጥቷል ወዳሉት ገዳም መመለሳቸውን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:20 0:00


XS
SM
MD
LG