በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የሴኔት የአብላጫዎች መሪ ሃሪ ሬይድ ሲዘከሩ


El exsenador demócrata Harry Reid en una foto de 1996.
El exsenador demócrata Harry Reid en una foto de 1996.

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የሴኔት የአብላጫዎች መሪና ኔቫዳን በመወከል በሴኔት ውስጥ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ አባልም የሆኑት ሃሪ ሬይድ በኔቫዳ ሄንደርሰን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን ባለቤታቸው ወ/ሮ ላውራ ሬይድ አስታውቀዋል፡፡ የባለቤታቸውን ዜና እረፍት ያስታወቁት ወ/ሮ ላውራ ባለቤታቸው ያለፉትን አራት ዓመታት በጣፊያ ካንሰር ሲሰቃዩ ቆይተው በሰላም አርፈዋል ብለዋል፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸውን በተመልከተ መርሃብሮች በመጪዎቹ ቀናት ይፋ እንደሚደረግም ነው አስታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ ላውራ “ሃሪ አፍቃሪ ቤተሰብ እና ታማኝ ጓደኛ ነበር...ባለፉት ዓመታት እየደረሱን ስላሉ ድጋፎች እናመሰግናለን፡፡ በተለይም ሲንከባከቡት ለነበሩት ሃኪሞች እና ነርሶች ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡

ሃሪ ሜሰን ሬይድ የቦክስ ተወዳዳሪ የነበሩ ሲሆን በኋላም የሕግ ባለሞያ ሆነዋል፡፡ በኮንግረስ ውስጥም በከፍተኛ የድርድር ክህሎታቸው የታወቁ ሰው ነበሩ፡፡ በዋሺንግተን ለ34 ዓመታት ከዘለቀው አገልግሎታቸው በኋላም ቢሆን በጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና በኋላም በባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን፤ አብላጫውን ሴኔት በመቆጣጠር እ.ኤ.አ በ2010 ሙሉ ለሙሉ ስፍራውን ለ ፐብሊካኖች እንስኪለቁ ድረስ ከጀርባ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ሬይድ እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ጡረታ ውጥተዋል፡፡

ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የሃሪ ሬይድን እረፍት ተከትሎ ባወጡት መግለጫ “ሃሪ አንድ ነገር እፈጽማለሁ ካለ ያደርገዋል” ሲሉ የረዥም ጊዜ የሴኔት ባልደረባቸውን አስታውሰዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊትም ልጃቸው ሮሪ ሬይድ እና ባለስልጣናት የላስ ቬጋስ አየርጣቢያን ሃሬ ሬይድ ዓለም አቀፍ አየር ጣቢያ በማለት እንዲሰየም አድርገዋል፡፡ የሁናን እሳቸውም ሆኑ ባለቤታቸው ላውራ ሬይድ በቦታው ሊገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ልጃቸው ሮሪ ሬይድ የክላርክ አውራጃ ኮሚሽን ሊቀመንብር እና የኔቫዳ የገዢዎች ተዋዳዳሪ ናቸው፡፡

ሬይድ በዋሺንግተን ለየት ባለ ጸባያቸው የሚታወቁ ፖለቲከኛም ናቸው፡፡ በተለየ መልኩም፥ ስልክ አነጋግረው ሲያበቁ ሳይሰናበቱ ስልኩን በመዝጋት ይታወቃሉ፡፡ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ 2019 ዓ.ም ፕሬዘዳንት እንኳን ሆኜ ስልኩን ሳይሰናበት ነበር የሚዘጋው ብለዋል፡፡

ሃሪ ሬይድ ብዙ ጊዜም በቀላሉ ሲገመቱ ለቀው የተገኙ ሰው ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገ ምርጫ የሪፐብሊካን ተመራጭ በነበሩት ሻሮን ኤንጅል ይሸነፋሉ በሚል በራሳቸው ፓርቲ አባላት ሳይቀር ተገምቶ የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን 50 ከመቶ ሻሮን ኤንጅል ደግሞ 45 ከመቶ ድምጽ በማምጣት ሊያሸንፉ ችለዋል፡፡ እሳቸውም ከኒዮርክ ታይምስ ጋር በዛኑ ዓመት ባነበራቸው ቃለ መጠይቅ “ታላቅ ተናጋሪ ነው፤ ቆንጆ ነው የሚሉ ሰዎች የሉኝም ነገር ግን እኔ ጉዳዬ አይደለም ባለሁበት እና ከታሪኬ ጋር ተስማምቼ የምኖር ሰው ነኝ” ብለዋል፡፡

በኔቫዳ የተወለዱት ሃሪ ሬይድ አባታቸው ከፍተኛ አልኮል ጠጪ የነበሩ በመሆናቸውን እራሳቸውን በማጥፋታቸው ላውንደሪ ቤት ከሚሰሩ እናታቸው ጋር በአነስተኛ በር በሌላት የጫካ ቤት ውስጥ ነው ያደጉት፡፡ የአሁኗን ባላቤታቸውን ላውራ ጓልድ ጋር በዩታ ዪኒቨርስቲ ተገናኝተው እ.ኤ.አ በ1959 ሊጋቡ ችለዋል፡፡ በኋላም በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል የሌሊት ተራ የፖሊስ ስራ እየሰሩ ትምህርታቸውን በመግፋት ከጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርስቲ በሕግ ተመርቀዋል፡፡

በ28 ዓመታቸው የኔቫዳ ምክርቤት ተመራጭ በ30ዓመታቸው ደግሞ ወጣቱ የኔቫዳ ምክትል ሃገረ ገዢ ሆነዋል፡፡

በሴኒት በነበራቸው ቆይታም እጅግ ብዙ ስራዎችን እንደሰሩ የሚነገርላቸው ሲሆን እ.ኤ.አ በ2016 ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ “እሱ ክጎኔ ባይኖር ኖሮ ብዙ ነገሮችን መፈጸም አልችለም ነበር” ሲሉ መስክረውላቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG