በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የህግ መወሰኛው ም/ቤት መሪ ኻሪ ሪድ አረፉ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የህግ መወሰኛ ም/ቤት መሪ የሆኑትና የኔቫዳ ግዛትን በመወክል ረጅሙን ጊዜ ያገለገሉት ሴናተር ኻሪ ሪድ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የህግ መወሰኛ ም/ቤት መሪ የሆኑትና የኔቫዳ ግዛትን በመወክል ረጅሙን ጊዜ ያገለገሉት ሴናተር ኻሪ ሪድ

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የህግ መወሰኛ ም/ቤት መሪ የሆኑትና የኔቫዳ ግዛትን በመወክል ረጅሙን ጊዜ ያገለገሉት ሴናተር ኻሪ ሪድ በ82 ዓመታቸው ትናንት ማክሰኞ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፡፡

ዴሞክራቱ ሴናተር ኻሪ ሪድ ለ32 ዓመታት በም/ቤቱ በቆዩባቸው ዓመታት ከተቀናቃኞቻቸው ጋር በጠንካራ ተደራዳሪነታቸው የሚታወቁ ሲሆን በበርካታዎቹ የአገሪቱ ህጎች ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ሰው እንደነበሩ ተነግሮላቸዋል፡፡

የምክር ቤቱን መሪነት በሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት በጆርጅ ደብለው ቡሽና እና በዴሞክራቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዘመን ይዘው የቆዩ ሰው ነበሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ህልፈታቸውን አስመልክተው ባወጡት መልዕክት ሪድ

“ቃላቸውን ከሰጡህ የምትተማምንባቸው ሰው ናቸው” ብለዋል፡፡

ኦባማ ኬር እየተባለ የሚጠራው ታሪካዊ የጤና አጠበባቅ ህግ ሲወጣም፣ የሌላኛው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ከሆኑት ናንሲፖሎሲ ጋር በመሆንን፣ ትልቁን ድርሻ የተጫወቱ ሰው መሆናቸው ተመስክሮላቸዋል፡፡

እኤአ በ2016 ስለ ሴናተሩ የመሰከሩት ፕሬዚዳንት ኦቦማ “እሳቸውን ከጎኔ ባይቆሙ ኖሮ ምንም ነገር ማከናወን አልችልም ነበር” በማለት መመስከራቸው ተመልክቷል፡፡

የሴንተር ኻሪ ሪድ የቀብር ሥነ ስርዓት የሚፈጽመበት እለት በቅር ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG