በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ጉባዔ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ቪዥን ኢትዮጵያ ያዘጋጀው "የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ በኢትዮጵያ" ተብሎ የተሰየመ የውይይት ጉባዔ የፊታችን ቅዳሜና ዕሁድ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ይካሄዳል።

ቪዥን ኢትዮጵያ ያዘጋጀው “የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ በኢትዮጵያ" ተብሎ የተሰየመ የውይይት ጉባዔ የፊታችን ቅዳሜና ዕሁድ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ይካሄዳል።

ቪዥን ኢትዮጵያ የዛሬ ሁለት ዓመት ተኩል አካባቢ በተወሰኑ ምሁራንና ባለሙያዎች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተቋቋመና የሚሠራው ለትርፍ ያልሆነ ሆኖ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የተመዘገበ ስብስብ ነው።

ቪዥን ኢትዮጵያ ከዚህ በፊትም ሦስት ስብሰባዎችን ያደረገ ሲሆን ጥቅምት 25/2008 ዓ.ም. የተደረገው የመጀመሪያው ስብሰባ በኢትዮጵያና በኤርትራ ግንኙነቶች ላይ አተኩሮ ተወያይቷል።

ሁለተኛው ስብሰባ በዚያው በ2008 ዓ.ም. መጋቢት 13 እና 14 ግጭትን በማስወገድና ከግጭት አወጣጥ ዘዴዎች ላይ መወያየቱንና ከሃያ በላይ ተናጋሪዎች የቀረቡበት ሦስተኛው ስብሰባ መስከረም 16 እና 17/2009 ዓ.ም. በሽግግር ላይ መነጋገሩን የውይይት መድረኩ አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የዘንድሮው መድረክ ተግባር ከግጭትና ከቀውስ የሚወጡ ሃገሮች እንዴት እንደወጡ ተሞክሯቸውን ማየትና መገምገም፤ ለኢትዮጵያ የትኛው መንገድ ይሻላል? የሚል ውይይትም ማካሄድ መሆኑን ፕሮፌሰር ሚንጋ አክለው ገልፀው መድረኩ ለማንም ክፍት መሆኑንና መገኘት የሚፈልጉና የሚችሉ ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ጉባዔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG