በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍቅረኞች ቀንን- የተቸገሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለመርዳት


ቢጫው ንቅናቄ በሚል የተደራጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመንገድ ላይ አበባ ሲሸጡ
ቢጫው ንቅናቄ በሚል የተደራጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመንገድ ላይ አበባ ሲሸጡ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመማር ዕድል አግኝተው ነገር ግን ከጥቃቅን መሰረታዊ ችግራቸው ጀምሮ እስከ ትምሕርት መርጃ መሳሪያዎች ማሟላት የማይችሉ ተማሪዎችን ለመርዳት የቢጫው ንቅናቄ በሚል የተደራጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ዕርዳታ በማሰባሰብ ሥራ ተጠምደዋል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ሥነ-ጽሑፍና የፎክሎር ትምሕርት ክፍል የአምስተኛ ዓመት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ ሆና ትምሕርቷን ለመጨረስ በመንገዳገድ ላይ ያለች ወጣት ታሪክም በዘገባው ተካቷል።

የዓመቱ ፌብሩዋሪ 14 በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር የሚቆጥሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥንዶች የቫላንታይንስ ዴይ ወይም የፍቅረኞች ቀንን የሚያከብሩበት ዕለት ነው። አሜሪካውያኖችም ለሚወዷቸውና ለፍቅር አጋሮቻቸው የተለያዩ ስጦታዎችን የሚሰጡበት ቀን ነው። እንደ ከረሜላ እና ቸኮሌት ያሉ ስጦታዎች በስጦታዎቹ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። የአሜሪካ የጅምላ ሽያጭ ፌደሬሽን ባወጣው ጥናት መሰረት በዚህ ዓመት ተጠቃሚዎች ለፍቅረኞች ቀን የቸኮሌት ግዢ 1.7 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያደረጋሉ።

ይህን የፍቅረኞች ቀን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በተለይ በአዲስ አበባና በአንዳንድ ዋና ዋና ከተሞች በወጣቶች ዘንድ በብዛት እየተከበረ ይገኛል።

ባልደረባችን ጽዮን ግርማ /The Yellow Movement/ ወይም የቢጫው ንቅናቄ በሚል የተደራጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይህን በዓል በተለየ ሁኔታ እያከበሩት ነው ትለናለች- በቀጣዩ ዘገባዋ።

የፍቅረኞች ቀንን- የተቸገሩ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለመርዳት
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:09 0:00

XS
SM
MD
LG