በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቨርጂኒያው ኪዳነ ምህረት ኮሮና እና የአቡነ ፋኑኤል አስተያየት


ፎቶ ፋይል፦ በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
ፎቶ ፋይል፦ በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል

በቨርጂኒያ ክፍለ ግዛት ኢትዮጵያውያን በብዛት ይኖሩበታልተብሎ በሚታወቀው የአሌክዛንድሪያ ካውንቲ ውስጥ በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የኮሮናቫይረስ ሥርጭት በመታየቱ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ የነበሩ አንዲት እህት ሲሞቱ 4 ካህናትና አገልጋዮችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው ታውቋል፡፡ በዚህ የተነሳም የአሌክዛንድሪያ መንግሥት ጤና መምሪያ ለቤተክርስቲያኑ ምእመናን እና ማኅበረሰቡ አንድ ማሳሰቢያ ልኳል፡፡

በነሀሴ 14-17 ባሉት ቀናት ውስጥ ወደዚህች ቤተከርስቲያን ህንጻ የገባ ሰው በሙሉ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጠ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

በመሆኑም በአስቸኳይ ራሱን ከምንም እንቅስቃሴ አቅቦ ለ14 ቀናት በቤቱ እንዲቀመጥና ራሱን ከበሽታው የህመም ምልክቶች እንዲያዳምጥም ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ደግሞ በኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን፣ በተለይ በዚህ ሰሞን፣ በተለያዩ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች በሚገኙ ቤተክርስቲያናትም ተመሳሳይ ችግሮች እየተከሰቱ መሆኑን ሪፖርት እየደረሳቸው እንደሆነ ገልጸው ማኅበረሰቡ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቨርጂኒያው ኪዳነ ምህረት ኮሮና እና የአቡነ ፋኑኤል አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:24 0:00


XS
SM
MD
LG