በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን አስተዳደር ታሪካዊ ፈተናዎች ይገጥሙታል


ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካምላ ሃሪስን
ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካምላ ሃሪስን

ብርቱ ፉክክር የታየበትን ምርጫ ካሸነፉ በኋላ፣ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ሙሉ ትኩረታቸውን፣ ክፉኛ ወደ ተከፋፈለችው፣ በወረርሽኝ ወደ ተመታችውና፣ ኢኮኖሚዋ እየተንገታገተ ወደምትገኘው አገራቸው በማዞር እንዴት አድርገው እንደሚያስተዳደሯት መላ መምታት ጀምረዋል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ብራየን ፓደን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በምርጫው ወቅት፣ ለድሆቹ ሠራተኞች፣ የጤና ሽፋንን በስፋት ለማዳረስ፣ ለሚሊዮኖች አዳዲስ ሥራዎችን የሚፈጥሩ፣ ንጹህ ኃይል ሰጭና አመንጭ ኢንደስትሪዎችን ለመከፈት፣ ቃል ገብተዋል፡፡ ከፊት ለፊታቸው ያለው አጣዳፊ ነገር ግን፣ የጆንስ ህፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ሆስቲፓል ባወጣው ዘገባ መሠረት ለ237ሺ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውና እየተስፋፋ የመጣው የኮረና ቫይረስን ስርጭት የመግታት ጉዳይ ነው፡፡ በድል ብስራታቸው ምሽት እሳቸውም ይህንኑ ተናግረዋል፡፡

"ይህን ወረርሽኝ ለማቆም እምቆጥበው ቁርጠኝነትም ሆነ ጥረት አይኖርም" ብለዋል፡፡

ባይደን፣ ባለፈው ሰኞ፣ የኮረና ቫይረስን ግብረኃይል አቋቁመዋል፡፡ ግብረኃይሉ፣ ምርመራዎችን ለማስፋፋት፣ ለጤናው ዘርፍ ሠራተኞች የመከላከያ መሣሪያዎችን ምርት ለመጨመር፣ ክትባቶችን ለማምረትና ስርጫታቸውንም ለማስፋት የሚቻልበትን መንገድ በማመቻቸት የሚሰራ ነው፡፡

ይሁን እንጂ፣ ባይደን ይህን አጀንዳቸውን በሥራ ላይ ለማዋል፣ ቀድሞውንም የተከፋፈለውንና፣ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዘመን ደግሞ፣ ይበልጥ የተስፋፋው ልዩነት፣ የሚፈጥርባቸውን መሰናልክ ለማለፍ፣ ከፍተኛ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

በደለዌር ዩኒቨርስቲ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት፣ ዴቪድ ሬድልዋስክ፣ የልዩነቱ ፈተና ከባድ መሆኑን እንዲህ ይገልጹታል

“ክፍፍሉ ጥልቅ ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ እየተፈወሰ እንደሚሄድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ፈውሱ ቶሎ የሚመጣ ነገር ግን አይደለም፡፡ በቀላሉ አይመጣም”

ባይደን፣ በተለይ በጆርጂያ ግዛት፣ በመጭው ጥር፣ በድጋሚ የሚካሄደው የሁለት ሴንተሮች ምርጫ ውጤት ፈቅዶላቸው፣ የሴኔቱ ቁንጮ ሆነው ሊቆዩ ከሚችሉትና፣ የምክር ቤቱን አጀንዳ ከሚወስኑት ከሪፐብሊካኑ ሚች መካኔል፣ ብርቱ ተቃውሞ ሊጠብቃቸው ይችላል፡፡ በቴክሳስ የኒቨርስቲ፣ የአሜሪካ ፖለቲካ ፕሮፌሰር የሆኑት ሻነን ኦብሪያን

“መካኔል ነገሮችን ያጠብቁና ለብዙ ግራ ዘመሞች አማራጭ መንገዶችን ያጠቡ ይሆናል” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩልም፣ ጆ ባይደን ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት በሴንተርነት፣ ከዚያም በኋላ፣ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር ም/ፕሬዚዳንት ሆነው በሠሩባቸው ጊዚያት፣ ጉዳዮችን አግባብተውና አስማምተው የመጨረስ ታሪክ እንዳላቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ያ ልምዳቸው፣ ከመካኔል እና ከሌሎቹ ጋር፣ አሁንም ያግዛቸው እንደሆነ፣ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡ በቨንደር ቢልት ዩኒቨርስቲ፣ የግንኙነት ፕሮፌሰር የሆኑት፣ ጄፍ ቤነት

“ያንን የመልካም የግንኙነት ታሪካቸውን ተጠቅመው ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ምናልባት የማናስበውን ትብብር ሊፈጠሩ ይችሉ ይሆናል፡:” በማለት ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ባይደን በጋራና በትብብር መስራት፣ ለጋራ ጥቅም የሚረዳ መሆኑን፣ አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡

“መሻሻል አሳይተን ወደፊት መራመድ እንድንችል ተቃናቃኞቻችንን እንደጠላታቶቻችን መመልከት ማቆም አለብን፡፡ እርስ በርስ ጠላቶች አይደለንም አሜሪካውያን ነን፡፡” ብለዋል፡፡

ባይደን፣ የዴሞክራቶች መሪም ቢሆኑ፣ በራሳቸው ፓርቲ በኩል ደግሞ፣ በመንግሥት የሚደጎም ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን፣ እንዲሁም የከባቢ አየር ለውጥን አስመልከቶ በርካታ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከሚፈልጉት ተራማጅ ዴሞክራቶች፣ ከፍተኛ ግፊት የሚደርስባቸው መሆኑም ተገምቷል፡፡

ወደ ግራው ጫፍ ርቀው ሄደዋል የሚባሉት፣ እንደ ኒዮርኳ የምክር ቤት አባል፣ አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ ኮርቴዝ የመሳሰሉት፣“መሃሉን ይዘዋል የተባሉት ዴሞክራቶች ከተመረጡ በበኋላ፣ ከሪፐብሊካኖች ጋር ስምምነት ለማድረግ፣ ተራማጅ አጀንዳዎችን ወደ ጎን እየተዋቸው ነው፣” በማለት ከወዲሁ መክሰስ ጀምረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የባይደን አስተዳደር ታሪካዊ ፈተናዎች ይገጥሙታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00


XS
SM
MD
LG