በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ የተስፋ ቃል ከፍተዋል


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከ100 በላይ አገሮች የተሰባሰቡ የዓለም መሪዎች በተገኙበት በስኮትላንዱ ግላስኮ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ትናንት ሰኞ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር አሜሪካ የዓለም የሙቀት መጠንን ለመቀነስ ያስቀመጠችውን አዲስ ግብ አብራርተዋል፡፡

“ዩናዩይትድ ስቴትስ ባላፈው ሚያዝያ ወር በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስቀመጥኩት ግብ መሰረት እኤአ በ2030 የልቀት መጠንን በ2005 ከነበረው የልቀት መጠን ከ50 እስከ 52 ከመቶ በታች በማድረግ ያሰበችውን ግብ ልታሳካ ትችላለች ብለዋል፡፡

“ለዓለም ማሳወቅ የምንፈልገው፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደመድረኩ መመለሷን ብቻ አይደለም፡፡ በአርአያነትም ምሳሌ በመሆን ትመራለች ብለን ተስፋ እንዳደርጋለን፡፡” ያሉት ባይደን በርግጥ “እስካሁን የሆነው እንደዚህ አለመሆኑ ይገባኛል፡፡ ለዚህም ነው የኔ አስተዳደር የአየር ንብረት ለውጥ ተግባር እንጂ ቃል አለመሆኑን ለማሳየት ሌት ተቀን እየሠራ የሚገኘው” በማለት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

እነዚያ አዳዲስ ግቦች፣ ቀደም ሲሉ በነበሩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ ተመስርተው የሚፈጸሙ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ስለ ቀውሱም ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችላቸው በጀት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ይህ በጀት የጠቅላላው የአየር ለውጥ እቅዳቸው አካል የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ እቅዳቸው ማስፈጸሚያ የ3ቢሊዮን ዶላርን ይጠይቃል፡፡ ባይደን ቃላቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የምክር ቤቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህ በተጨማሪም ባይደን በአገር ውስጥ በማተኮር፣ እኤአ በ2030 የአረንጓዴ ጋዝ ልቀትን ከ 1ጊጋ ቶን በላይ ለመቀነስ የአሜሪካን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የሚያግዙ ህጎችን ማውጣት ይኖርባቸዋል፡፡

እነዚህ ህጎች ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ውስጥ ለወራት ተቀምጠዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በብዙ ቢደራደሩባቸውም ባይደን ወደ ጉባኤው ከመሄዳቸው በፊት ሊደርሱ አልቻሉም፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ እኤአ በ2017 ከፓሪስ ስምምነት ለመውጣት በወሰኑት መሰረት፣ እኤአበ2020 ጠቅልላ ብትወጣም ፣ ባይደንወደ ስምምነቱ የተመለሱት ሥልጣን በያዙ የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡

ይህም ሆኖ አንዳንድ ተችዎች ሌሎች አገሮች ለአየር ንብረት ቀውሱ ካሳዩት ቁርጠኝነት አንጻር ሲታይ፣ የባይደን አስተዳደር ያሳየው ቁርጥኝነት ያነሰ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ባይደንም በጉባኤው ላይ ያልተገኙት ቻይናና ሩሲያ፣ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልከቶ ባሳዩት የቁርጠኝነት ማነስ ማዘናቸውን ገልጠዋል፡፡

XS
SM
MD
LG