በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤ ተጀመረ


የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በስኮትላንድ ግላስኮ ለመሳተፍ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ሥፍራው ተጉዘዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በስኮትላንድ ግላስኮ ለመሳተፍ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ሥፍራው ተጉዘዋል።

ከ100 በላይ የዓለም መሪዎች ዛሬ ሰኞ ለሁለት ሳምንት በሚቆየው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተካፋይ ለመሆን ተሰባስበዋል፡፡

ዋነኛው አጀንዳቸው ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ብክለት መቀነስና ታዳጊ አገሮች የአየር ንብረት ቀውስን ለዋጋት የሚያደርጉትን ጥረት በገንዘብ ለመደገፍ የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

በስኮትላንድ ግላስኮ የሚካሄደው ጉባኤ አስተናጋጅ፣ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ ከጉባኤው በፊት ከጽ/ቤታቸው በወጣው መግለጫ የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃን አስመልክቶ “ሰብአዊነት ለረጅም ጊዜ ሲጠባበቅ ቆይቷል” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

ጆንሰን በመግለጫው “ዛሬ እኛ ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት ካልሰጠነው ለነገዎቹ ልጆቻችን በጣም የረፈደ ይሆናል” ብለዋል፡፡

ከዛሬው ስብሰባ በፊት የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ንብረት ልዑክ ጆን ኬንሪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የጉባኤው ዓላማ ፣ የዓለም የሙቀት መጠንን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች በማውረድ ከቅድመ ኢንደስትሪ በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስና ለአስርት ዓመታት እንዲቆይ የሚፈለገውን የዓለም አቀፉንትልም ማሳከት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የቻይናና ሩሲያ መሪዎች በጉባኤው ላይ አልተገኙም፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ “ሩሲያና ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ቁርጠኝነት አለማሳየታቸውን ያመለክታል፣ ይህ በጣም ያስዝናል” ሲሉ ትናንት እሁድ በተካሄደው የቡድን 20 አባላት አገራት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG