በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢላን መስክ ወፏን በድንገት አበረሩ


ኢላን መስክ ባለፈው ዓመት በ44 ቢሊዮን ዶላር የገዙት ትዊተር ምልክት የሆነችውን ሰማያዊዋን ወፍ፣ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ወደ “X” ምልክት ቀይረዋል።
ኢላን መስክ ባለፈው ዓመት በ44 ቢሊዮን ዶላር የገዙት ትዊተር ምልክት የሆነችውን ሰማያዊዋን ወፍ፣ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ወደ “X” ምልክት ቀይረዋል።

ኢላን መስክ ባለፈው ዓመት በ44 ቢሊዮን ዶላር የገዙት ትዊተር ምልክት የሆነችውን ሰማያዊዋን ወፍ፣ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ወደ “X” ምልክት ቀይረዋል። የማኅበራዊ መገናኛ መድረኩን በዐዲስ መልክ ለማዋቀር ከወሰዱት ርምጃዎች ትልቁ ነው ተብሏል።

አዲሱ የ”X” ምልክት በኮምፒውተሮች ላይ ባሉ የትዊተር መተግበሪያ ላይ ከሰኞ ጀምሮ የታየ ሲሆን፣ በእጅ በስልክ ላይ ባለ የትዊተር መተግበሪያ ላይ ግን ሰማያዊዋ ወፍ አሁንም በመታየት ላይ ነች፡፡

በሳን ፍርራንሲስኮ የትዊተር ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ ላይ ያለችውን የኩባንያው ሰማያዊ ወፍ ምልክት ሠራተኞች ትናንት ሰኞ በማንሳት ላይ ሳሉ፣ ፖሊስ አስቁሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ፣ አስፈላጊውን ፈቃድ ባለማውጣታቸውና፣ ከሕንጻው ላይ የሚወድቅ ፍርስራሽ ከታች አላፊ ሰዎችን እንዳይጎዳ ከለላ አልታደረገም በሚል ነው።

የትዊተር ምልክት የሆነችው ሰማያዊ ወፍ ከሕንጻውም ሆነ ከመተግበሪያው ላይ ድንገት በጥድፊያ መነሳቷ፣ ኢላን መስክ እያመነቱ ትዊተርን ከገዙበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ኩባንያውን ለማስተዳደር የሚከተሉት ትርምስ የተሞላበት አመራር አካል እንደኾነ ተነግሯል።

“ወደፊት ለትዊተር ዋጋ ያለው ልዩ መለያ ወይም ብራንድ የለም። ስለዚህ ኢላን መስክ አንዳች ነገርን በማጥፋት የሰዎችን ትኩረት በፍጥነት ለማግኘት እየሞከሩ ነው፣” ሲሉ የኮርፖሬት ብራንድ ኤክስፐርት የሆኑት አለን አዳምሰን ይናገራሉ። “በዚህም ኩባንያውን ወዴት እየወሰዱ እንደሆነ ትኩረት እንዲያገኝ ይሞክራሉ። በትዊተር ላይ የሚደረገው የነፍስ አድን ሥራ ረጅም ግዜ የሚፈጅ ነው፣ እርሳቸው ግን በፍጥነት ለማድረግ እየሞከርሩ ነው፣” ሲሉ አክለዋል አዳምሰን።

መስክ ተከታዮቻቸውን አዲስ የሎጎ ወይም የምልክት ሃሳብ እንዲያቀርቡ እሁድ ምሽት ጋበዙ። ‘ብዙም የአርት ሥራ የማይጠይቅ ነው፣ ግን የተሻለ ማድረግ ይቻላል’ ብለው የ”X” ምልክትን ሰኞ መረጡ።

የራሳቸውን የትዊተር አካውንት ምልክት በ”X” ቀይረው፣ በሳን ፍራንሲስኮ በሚገኘው ዋና መ/ቤቱ ሕንጻ ላይም፣ በመብራት ምልክቱ እንዲንጸባረቅ አደረጉ።

ይህም፣ መስክ የትዊተር ተጠቃሚዎችን እና ማስታወቂያ አስነጋሪዎችን እንዲገለሉ ከደረጉ እርምጃዎቻቸው አንዱ ነው ተብሏል። እርምጃው ከአዲስ ተፎካካሪዎቻቸው፣ በተለይም የበፌስቡኩ እናት ኩባንያ ሜታ አገልግሎት ላይ ያዋለው እና፣ በቀጥታ የትዊተር ተጠቃሚዎችን ኢላማ ካደረገው “Threads” ከተሰኘው አዲስ መተግበሪያ ለሚመጣው ፉክክር ተጋላጭ አድርጓችዋል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG