በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትዊተር የወፏን ምልክት በ”X” ሊቀይር ነው


ፋይል ፎቶ (ሮይተርስ)
ፋይል ፎቶ (ሮይተርስ)

ኢላን መስክ የትዊተር ምልክት የሆነችውን ወፍ በ “X” ምልክት እንደሚቀሩየር ዛሬ ሌሊት በዛው በትዊተር መልዕክታቸው አስታውቀዋል።

መስክ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ትዊተርን ከገዙ በኋላ፣ በተከታታይ ካደረጓቸው ለውጦች ይህ አዲሱ መሆኑ ነው።

ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በለቀቋቸው ተከታታይ የትዊተር መልዕክቶች፣ መስክ ከነገ ጀምሮ ምልክቱን ወድ “X” ሊቀይሩ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

“በቅርቡ የትዊተርን ልዩ መለያ የሆነውን ሁሉ እንሰናበታለን፣ ቀስበቀስም ወፎቹን በሙሉ” ብለዋል መስክ በትዊተር።

መስክ በየግዜው የሚወስዱት እርምጃ ማስታወቂያ አስነጋሪዎችን እያሸሸ እና የኩባንያው ገቢም እንዲቀንስ እንዳደረጋ እርሳቸውም አልሸሸጉም። ያንን ሁኔታ ለመቀየርም በቅርቡ አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ሾመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG