በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለሶሪያ ተቃዋሚዎች የምትሰጠውን ድጋፍ ልታቋርጥ ይሆን?


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የእሥላማዊ መንግሥት ቡድንን ሽንፈት ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው ከሽብሩ ቡድን ጋር ሲፋለሙ ለነበሩ ቡድኖች ስትሰጥ የቆየችውን ድጋፍ እየቀነሰች መሆኗን ዋይት ሃውስ ትናንት አስታውቋል።

የእሥላማዊ መንግሥት ቡድንን ሽንፈት ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው ከሽብሩ ቡድን ጋር ሲፋለሙ ለነበሩ ቡድኖች ስትሰጥ የቆየችውን ድጋፍ እየቀነሰች መሆኗን ዋይት ሃውስ ትናንት አስታውቋል።

ይህ የፖሊሲ ለውጥ ባለፈው ሣምንት ቀድሞ የተሰማው ከአንካራ ነበር።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ከቱርኩ አቻቸው ራሲፕ ታዪፕ ኤርዶዋን ጋር በስልክ ማውራታቸውንና ሶሪያ ውስጥ የሚገኙ የቱርክ አማፂያንን ማስታጠቃቸውን እንደሚያቆሙ ሚስተር ትረምፕ ቃል መግባታቸውን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ አስታውቀዋል።

ምንም እንኳ እሥላማዊ መንግሥት ቡድን እየተሸነፈ በመሆኑ ዩናይትድ ስቴትስ ከቡድኑ ጋር ሲዋጉ አጋሯ ሆነው ለቆዩ የአካባቢው ቡድኖች ስትሰጥ የቆየችውን ድጋፍ ልትቀንስ በምትችልበት ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ኸከቢ ሳንደርስ ትናንት ቢናገሩም ትረምፕ ለኤርዶዋን የገቡት ቃል ይኑር አይኑር ግን አላረጋገጡም ወይም አላስተባበሉም።

የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢናሊ ዪልድሪም ከእንግሊዝ የዜና አውታር - ቢቢሲ ጋር ትናንት ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “ለቱርክ ቁም ነገሯ የሆነውን ነገር ሚስተር ትረምፕ ተረድተውታል። እሥላማዊ መንግሥት ቡድንን በመዋጋት በኩል የቱርክ ፖሊሲ ከጅምሩ አንስቶ ግልፅ ነበር፤ እሥላማዊ መንግሥት ቡድንን መፋለም የምትፈልጉ ከሆነ ትክክለኛ አጋር መምረጥ አለባችሁ ነው ስንል የነበርነው። አንድን የሽብር ቡድን በሌላ የሽብር ቡድን መዋጋት አይቻልም” ብለዋል። “የፕሬዚዳንት ትረምፕን ውሣኔ” እንደሚያደንቁም ተናግረዋል።

የኩርድ ነፃ ኃይል የሚባለው የሶሪያ ኩርዶች ቡድን የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አብዱል ካሪም ኦማር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ዩናይትድ ስቴትስ ኩርዶችን ጨምሮ ሶሪያ ውስጥ ላሉ የተቃዋሞ ቡድኖች በምትሰጠው ድጋፍ ላይ የፖሊሲ ለውጥ አለማድረጓን ተናግረዋል።

ሦሪያ ውስጥ የሚገኙ መደበኛ ኩርዶች ግን በዩናይትድ ስቴትስ አቋም ላይ እምብዛም እምነት ያላቸው አይመስሉም። ቪኦኤ ያነጋገራቸው አንድ ቃሚሽሊ የምትባል ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ኩርድ “አሜሪካዊያን እዚህ የሚፈልጉት ነገር እንዳለቀ ለኩርድ ዋይ.ፒ.ጂ. የሚሰጡትን ድጋፍ ያቆማሉ ብዬ ነው የማምነው። እናም እዚህ ያሉ የተጨቆኑ ሕዝቦችን ለአምባገነኖች ጥለው ይሄዳሉ” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አሜሪካ ለሶሪያ ተቃዋሚዎች የምትሰጠውን ድጋፍ ልታቋርጥ ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG