ዋሽንግተን ዲሲ —
የቡሩንዲ ተፋላሚ ወገኖች ባስቸኳይ ውጊያ አቁመው ችግሮቻቸውን በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስገነዘበ።
የሰላሙን ጥረት በሚያደናቅፉና ሁከቱን ያሚያባብሱ ግለሰቦች የባንክ አካውንቶቻቸው እንዳይንቀሳቀስና የጉዞ እገዳ እንዲጣልባቸው ያስችላልል የተባለውን አዲሱን ረቂቅ ውሳኔ፥ 15ቱም የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ደግፈዋል።
ረቂቅ ውሳኔው በተጨማሪ፥ ለቡሩንዲ ሕዝብ የሚያስፈልገውን እርዳታ የሚገመግም የፖሊሲና የፀጥታ ጥበቃ ባለሞያዎች ጓድ እንዲመደብ ይፈቅዳል።
በቡሩንዲ፥ ሁከቱ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ የተቀሰቀሰው፥ ፕሬዘዳንቱ ፒየር ኩሩንዚዛ ለሦስተኛ ዙር የሥራ ዘመን በምርጫው ለመወዳደር ከወሰኑ በሁዋላ ነው።
ተቃዋሚዎች ፕሬዘዳንቱ የወሰዱት እርምጃ፥ ”ሕገ-መንግሥቱን የጣሰ ነው” ብለዋል።
ሙሉውን ዝርዝር አዳነች ፍሰሃየ አጠናቅራዋለች ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።