በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በኦዴሳ ወደብ ላይ የእህል ማጓጓዣዎች ላይ ጥቃት አደረሰች


ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን በሚገኘው ኦዴሳ ወደብ እና በዋና ከተማዋ ኪቭ ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ማድረሷን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡
ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን በሚገኘው ኦዴሳ ወደብ እና በዋና ከተማዋ ኪቭ ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ማድረሷን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡

ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን በሚገኘው ኦዴሳ ወደብ እና በዋና ከተማዋ ኪቭ ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ማድረሷን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡

የዩክሬን የጦር ኃይል እንዳስታወቀው የሩስያ ድሮኖች በወደቡ ላይ ያደረሱት ጥቃት የእህል ጭነት ማንሻ እና ሌሎች የኢንዱስትሪና የወደብ ድርጅቶች ላይ ቃጠሎ አድርሷል፡፡

የኦዴሳ ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ ኦሌ ኪፐር “የሩሲያ አሸባሪዎች እንደገና በወደቦች፡ በእህል እና በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ ጥቃት አድርሰዋል” ሲሉ ወንጅለዋል፡፡ በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ግን እስካሁን የወጣ ዘገባ የለም፡፡ ሩስያ በቅርቡ የዩክሬን የእህል አቅርቦት ወደ ዓለም ገበያ እንዲወጣ ካስቻለው የጥቁር ባሕር ስምምነት ከወጣች ወዲህ በተደጋጋሚ ኦዴሳ ወደብ ላይ የሚገኙ የእህል ማጓጓዣ ስፍራዎችን ደብድባለች፡፡

ሞስኮ ከስምምነቱ ከመውጣቷ በፊት “የራሷን የእህል እና የማዳበሪያ አቅርቦት ለማጓጓዝ ሁኔታዎችን የሚያመቻቸው ስምምነት ተግባራዊ አልሆነም” የሚል ቅሬታ አሰምታ ነበር፡፡

ሩሲያ ከኦዴሳ ወደብ ሌላ የጥቁር ባህር ስምምነት አለመታደሱን ተከትሎ በአማራጭ ማጓጓዣነት እያገለገሉ ያሉ የዩክሬን የወንዞች ወደቦችንም አጥቅታለች፡፡

ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደኪቭ ተቃርበው የነበሩትን ከአስር የሚበልጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አውድመናል”

በተያያዘ ዜና የዩክሬን ኅይሎች የአየር ጥቃት መከላከያ ኅይሎች ሌሊቱን ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ ኢራን ሰራሽ ሻሂድ ድሮኖች መትተው መጣላቸውን በኪቭ የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ “ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደኪቭ ተቃርበው የነበሩትን ከአስር የሚበልጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አውድመናል” ሲሉ ባለስልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

የሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ስብርባሪ በተለያዩ የከተማይቱ አካባቢዎች ጉዳት ማድረሱን የኪቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ተናግረዋል፡፡ በሰው ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆን ግን ለጊዜው የተሰማ ነገር የለም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG