በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በካታርና በጎረቤቶቿ ጉዳይ


ካታር ከጎረቤቶቿ ጋር ለገባችበት የዲፕሎማሲ ቀውስ መፍትኄ ለመፈለግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከካታርና ከቀሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከትናንት በተስያ ማክሰኞ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ካታር ከጎረቤቶቿ ጋር ለገባችበት የዲፕሎማሲ ቀውስ መፍትኄ ለመፈለግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከካታርና ከቀሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከትናንት በተስያ ማክሰኞ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ምንም እንኳ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምች ካታር ሽብር ፈጠራን በገንዘብ ትደግፋለች ሲሉ ቢከስሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትራቸው ቲለርሰን ግን ወገኖቹ ለንግግር እንዲቀመጡ እየገፋፉ ነው፡፡

መንበረ ርዕሰ-ብሄሩን ከተረከቡ ወዳህ የመጀመሪያ በሆነ የውጭ ጉብኝታቸው ሳዑዳ አረቢያን ባለፈው ወር የጎበኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ካታርና ጎረቤቶቿ የገቡበትን ቀውስ ገምግመዋል፡፡

«ካታር በሚያሳዝን ሁኔታ ለሽብር ፈጠራ የገንዘብ ድጋፍ ሰጭ ሃገር ሆና ቆይታለች፡፡ የባህረ ሰላጤው ሃገሮች ትብብር ምክር ቤት ለጉባዔ ከመቀመጡ በፊት መሪዎቹ አንድ ላይ ሆነው በፀባይዋ ምክንያት ከካታር ጋር ስለመጋጨታቸው ነግረውኛል፡፡» ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ባህሬን፣ ግብፅና ሌሎችም አረብ መንግሥታት ከዶሃ ጋር የነበራቸውን ዳፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጠው ከካታር ጋር የየብስ፣ የአየርና የባህር መገናኛዎችን ሁሉ አቁመዋል፡፡

የግጭቱና የግንኙነቶቹ መበላሸት ሰበብ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ካታር ከኢራን ጋር የቅርብ ግንኙነት ፈጥራ የሁከት ቡድኖችና እንቅስቃሴዎችን ትረዳለች የሚል ይገኝበታል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አሜሪካ በካታርና በጎረቤቶቿ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG