በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋለው ንትርክ በቀለጠው የላስ ቬጋስ መንደር


የዩናይትድ ስቴስ የ2016ዓ.ም. ፕሬዚዳንታዊ ክርክር ላስ ቬጋስ ኒቫዳ
የዩናይትድ ስቴስ የ2016ዓ.ም. ፕሬዚዳንታዊ ክርክር ላስ ቬጋስ ኒቫዳ

ዩናይትድ ስቴትስ አርባ አምስተኛውን ፕሬዚዳንቷን ለመምረጥ ጥድፊያ ላይ ትገኛለች፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ ሂላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ በየፊናቸው የሚያደርጉት የ“ምረጡኝ” “እኔ እሻላለሁ” ሩጫና ዘመቻ የመጨረሻው ጡዘት ላይ ደርሷል፡፡

ሁለቱ ዕጩዎች በዚህ የምርጫ ዘመን እንዲያካሂዱ ተይዞላቸው በነበረ መርኃግብር መሠረት ሦስት እሰጥ አገባዎቻቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ጊዜ ትናንት ምሽት፤ በምሥራቁ ሰዓት ደግሞ ዛሬ ማለዳ ላይ የተካሄደው ክርክር እጅግ የተሟሟቀ ነበር፡፡

ኔቫዳላስ ቬጋስ እንዲሁም የቀለጠው መንደር፤ እንዲሁም የኃጥዓን ምድር እየተባለች ነው የምትጠራው፡፡

የትናንት ምሽቷ ላስ ቬጋስ ግን ግለቷ የተለየ ነበር፡፡

​የወትሮው የቁማር ግርግር አልነበረም ሰንጎ የያዛት፤ የወትሮ ንግዷና የብሯ ጋጋታ አልነበረም የሰዉን ቀልብ ሰቅዞ ያመሸው፡፡

ባለፉ ሁለት ተከታታይ እሰጥ አገባዎች በተቀናቃኛቸው ሂላሪ ክሊንበን በሰፋ ልዩነት መሸነፋቸው የተነገረው ዶናልድ ትራምፕ ያለጥርጥር ማሸነፍ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

በመርኃ ግብሩ ከተያዘው ከዘጠና ደቂቃዎች ጥቂት ዘልቆ በሄደው የበረታ ትንቅንቅ፣ የቃላት፣ የክሥ፣ የራስ ውጤት ማስመዝገቢያ እንካሠላንቲያ ሁለቱም ዕጩዎች አዳዲስ ድምፆችን ለመሸመት ጥረዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ በፌስቡክ ቀጥታ ሥርጭት የንትርኩን ሂደት ሲከታተልና ለተመልካችና ለአድማጭ ሲያቀርብ ነበር፡፡

በአማርኛው የፌስ ቡክ ቀጥታ ሥርጭት ላይም ሁለት የኢትዮጵያ ግዩራን የሆኑ አሜሪካዊያን ምሁራን ቀርበው ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የጋለው ንትርክ በቀለጠው የላስ ቬጋስ መንደር
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:46 0:00

በፌስቡክ ላይቨ የተላለፈውን የምሁራኑን ትንታኔ ማዳመጥ ከፈለጉ ከታች የተያያዙትን ማገናኛዎች ተጭነው ይከተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG