በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ሶሪያ መላክ ላይ ለፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩ የሰጡት አስተያየት


ዋሽንግተን (Wahingtio) ልዩ ወታደራዊ ሃይል ወደ ሶሪያ ለመላክ መወሰንዋ ከተነገረ ካለፈዉ አርብ ወዲህ እያነጋገረ ነዉ፥ ከተለያዩ የጾርነት ቀጠናዎች የአሜሪካን ወታደሮች በማስወጣት ለሚታወቀዉ የኦባማ አስተዳደር አንጻራዊ እርምጃ ነዉ ተብሏል።

የፕሬዚደንት ኦባማ አስተዳደር እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራዉን ነዉጠኛ ቡድን የሚወጉ ሃይሎችን ለማሰልጠንና ለመርዳት 50 አባላት ያሉት የአሜሪካ ወታደሮች ለመላክ ያደረገዉ ዉሳኔ ለፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩ የሁለቱም ፓርቲ አባላት ዘንድ የክርክር ነጥብ ሆኖአል። እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2017 ዓም በፕሬዚደንትነት ኦባማን ለመተካት ከሚወደደሩት ዴሞክራቶችም ሆነ ሬፑብሊካዉያን አባላት ሃሳቡ እሰዬዉ የተባለለት አልሆነም። ከሬፑብሊካን በኩል ሴናተር ማርኮ ሩብዮ(Marko Rubio) ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ደግሞ ሴናተር Bernie Sanders እና ሴናተር Hilary Clinton በጉዳዩ ላይ ስላላቸዉ አመለካከት ማይክል ቦውማን (Michael Bowman) አጠናቅሯል። ትዝታ በላቸዉ አዘጋጅታለች ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ሶሪያ መላክ ላይ ለፕሬዚደንት የሚወዳደሩ የሰጡት አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG