በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መነንዴዝ ሌላ ክስ ቀረበባቸው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ባለሥልጣናት የህዝብ እንደራሴ ሴናተር ባብ መነንዴዝ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ባለሥልጣናት የህዝብ እንደራሴ ሴናተር ባብ መነንዴዝ

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ባለሥልጣናት የህዝብ እንደራሴው ሴናተር ባብ መነንዴዝ የካታር ንጉሣዊ ቤተሰብ አባልን በቤቶች ግንባታ (ሪል እስቴት) ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ከሚፈልጉ አንድ የኒው ጀርሲ ነጋዴ ጋር አስተዋውቀዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል፡፡

ማንነታቸው ያልተገለጸው የካታሩ ንጉሣዊ የቤተሰብ አባል በካታር ኢንቨስትመንት ኩባንያ ውስጥ ኃላፊ እንደነበሩ ሲገለጽ ኢንቨስትመንቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የፈጀ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

በማንሃታን ፌደራል ፍርድ ቤት የቀረበው ይህ የቅርብ ጊዜው ክስ በዲሞክራቱ እንደራሴ እና በባለቤታቸው እንዲሁም በሶስት ነጋዴዎች ላይ የቀረበ ክስ ሲሆን ሁሉም ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል ።

አሁን የተመሰረተው ክስ ቀደም ሲል መነንዴዝና ባለቤታቸውን ጥሬ ገንዘብ፣ ብዛት ያለው ወርቅ፣ እንዲሁም የቅንጦት ተሽከርካሪዎችን በጉቦ መልክ ተቀብለዋል በሚል ተመስሮባቸው በነበረው ክስ ላይ ተጨማሪ ሆኖ የቀረበ ክስ መሆኑ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG