በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንደራሴው እና ባለቤታቸው በጉቦ ተከሰሱ


የኒው ጀርሲ እንደራሴ ባብ ሜኔንዴዝ
የኒው ጀርሲ እንደራሴ ባብ ሜኔንዴዝ

በድጋሚ የታደሰ

የኒው ጀርሲ እንደራሴ የሆኑት ባብ ሜኔንዴዝ እና ባለቤታቸው በቤታቸው በተደረግ ፍተሻ 1 መቶ ሺሕ ዶላር የሚያወጣ ወርቅ እና 480 ሺሕ ዶላር ጥሬ ገንዘብ መገኘቱን ተከትሉ በጉቦ መከሰሳቸውን የፌዴራል አቃቢያን ህጎች አስታውቀዋል።

ዛሬ ዓርብ ይፋ በሆነው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ባብ ሜኔንዴዝ በውጪ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ እንዲያደርጉ፣ የግብጽን ፈላጭ ቆራጭ መንግስት ተጠቃሚ ማድረግን ጨምሮ፣ ሌሎችንም የሙስና ተግባራት ፈጽመዋል ለዚህም ጥሬ ገንዘብ፣ ወርቅ እና ቅንጡ መኪናዎችን ተቀብለዋል ተብሏል።

የ69 ዓመቱ ባብ ሜኔንዴዝ እና የባለቤታቸው ክስ የመጣው፣ ከስድስት ዓመታት በፊት የመንግስት ባለሥልጣናት ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ከአንድ ሐኪም ውድ ስጦታ ተቀብለዋል የሚለው ክስ ከሕዝብ የተውጣጡት ዳኞች ለሁለት ተከፍለው ውሳኔ ላይ ሳይደረስ መቅረቱን ተከትሎ ነው።

ሜኔንዴዝ በሁለት የተለያዩ ጉዳዮች የተከሰሱ የመጀመሪያው እንደራሴ ናቸው ሲል የሴኔቱ ታሪካዊ ጉዳይዮች ቢሮ አስታውቋል።

ሴኔቱን በጠባብ ብልጫ የሚመራውን የዲሞክራቲክ ፓርቲ የሚወክሉትና ላለፉት 30 ዓመታት በዋሽንግተን ሲሰሩ የቆዩት ሜኔንዴዝ፣ በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የሚጠብቃቸዋል።

ከትውልደ ኩባ ቤተሰብ የተገኙት ሜኔንዴዝ፣ ከእ.እ.አ 1986 ጀምሮ በኒው ጀርሲ ግዛት እና በዋሽንግተን በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነት ላይ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG