በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤልጂግ የጸረ ሽብር አያያዝ የረዥም ጊዜ ስጋት እንዳንጸባረቀ ተገለጸ


ብራሰልስ ላይ የአሸባሪዎች ጥቃት ከተፈጸመ ወዲህ የሀገሪቱ የጸረ ሽብር አሰራር በአለም ዙርያ እየተነቀፈ ነው።

ብራሰልስ ውስጥ በተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት የሚጠረጠሩ ሰዎች ፍለጋ በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት ከየአቅጣጫው ነቀፌታ እየቀረበ በመሆኑ የሀገሪቱ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ጃን ጃምቦን ከስልጣናቸው ለመሰናበት ጠየቁ።

“ነገሮችን በጥሞና ስንመለከት በተለያዩ ዘርፎች አብይ ጥያቄዎች ማንሳት ይቻላል። ስለ ፍርድ ሚኒስቴር፣ ስለ ተከተለው ሁኔታና ስለ ፖሊስ ሃይል ጥያቄ ያስነሳል።”ብለዋል።

ከአጥፍቶ ጠፊዎቹ አንዱ አምና ሀምሌ ወር ላይ ከቱርክ አባረን ወደ ቤልጂም እንደላክነው ለሀገሪቱ ባለስልጣኖች አስታውቀን ነበር። እነሱ ግን ለቀቁት ሲሉ የቱርክ ፕረዚዳንት ነቅፈዋል።

አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣኖችም ነቅፈዋል። ከዘጠኝና ከስር አመታት በፊት በማድሪድና በለንደን የተፈጸሙት የሽብር ጥቃቶችን መሰረት በማድረግ በበልጅምም ሆነ በሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ለቀቅ ያለው አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ነው የአሜሪካ ባለስልታኖቹ የተናገሩት።

የአውሮፓ ኮሚሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንት ፍራንስ ቲመራማስ ታድያ የቀረቡትን ህሳቦች ለመተግበር መፍጠን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

“ያቀረብናቸውን ሃሳቦች ለመተግበር የሚያስችለን ገንዘብ የምናገኝበት መንገድ ማፋጠን አለብን። አሸባሪዎች ክረዲት ካርዶችንና የአስቀድሞ ክፍያ ካርዶችን ለመጥቀም እንዳይችሉ ለማደረግና መሳርያዎች የሚቀመጡባቸውን ቦታዎች ለይተን ለማወቅ የሚያስችለን ገንዘብ ማግኘት ያስፈልገናል።”ብለዋል።

በአውሮፓ አዲስ የጸረ-ሽብር ማዕከል መመስረቱ ችግሩን ለመቋቋም ይረዳል የሚል ተስፋ ቢኖርም በርካታ የወቅቱና የቀድሞ የጸረ-ሽብር ጥረት ባለስልጣኖች ነቅቶ መከታትል የሚያስፈልግበት ጊዜ የዘገየ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የብሄራዊ ጸጥታ ዘጋቢ ጀፍ ሰድሊን ዝርዝር ዘገባ አለው አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

የቤልጂግ የጸረ ሽብር አያያዝ የረዥም ጊዜ ስጋት እንዳንጸባረቀ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG