በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ 14 የሁቲ ሚሳዬሎችን አወደመች፣ ድርጅቱንም በሽብርተኝነት ፈረጀች


ፎቶ ፋይል፦ የሁቲ ተዋጊዎች እና ጎሳዎች የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የባሕር ኃይሎች የፈፅሟቸውን ድብደባዎች በመቃወም የሁቲ አማፂያን በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሰልፍ ወጥተው፤ ሰንዓ፣ የመን እአአ ጥር 14/2024
ፎቶ ፋይል፦ የሁቲ ተዋጊዎች እና ጎሳዎች የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የባሕር ኃይሎች የፈፅሟቸውን ድብደባዎች በመቃወም የሁቲ አማፂያን በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሰልፍ ወጥተው፤ ሰንዓ፣ የመን እአአ ጥር 14/2024

አሜሪካ 14 የሚሆኑና በየመን የሁቲ አማፂያን በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ለመተኮስ ተዘጋጅተው የነበሩ ሚሳኤሎችን ማውደሟን ትናንት አስታውቃለች፡፡

በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ፣ አሜሪካ በድጋሚ ድርጅቱን በሽብተኛ ድርጅትነት ፈርጃለች፡፡

“ሚሳዬሎቹ በማንኛውም ሰዓት ሊተኮሱ ተዘጋጅተው የነበሩ ሲሆን፣ በአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦችም ሆነ በሌሎች የንግድ መርከቦች ላይ ስጋት የደቀኑ በመሆናቸው፣ የአሜሪካ ኃይሎች ራሳቸውን የመከላከል መብት እና ግዴታቸውን ተጠቅመዋል” ሲል የአሜሪካው ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ባወጡት መግለጫ፣ “አንሳራላ” ወይም በዘልማድ ሁቲ ተብለው የሚጠሩትን አማጺያን፣ ከሰላሳ ቀን በኋላ ጀምሮ በሽብርተኝነት ትፈርጃለች ብለዋል። ባሉት ሰላሳ ቀናት ውስጥ፣ አሜሪካ ከባለ ድርሻ አካላት፣ ረድኤት ድርጅቶች እና አጋሮች ጋር በመሆን ሰብዓዊ ርዳታ እና አስፈላጊ የሆኑ የንግድ ሸቀጦች አገሪቱ እንድታገኝ ታደርጋለች ሲሉም አክለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ሁቲዎች ጥቃታቸውን የሚያቆሙ ከሆነ፣ አሜሪካ ፍረጃውን እንደገና እነድምታጤነው ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪው ጄክ ሰለቨን ተናግረዋል።

የሁቲ አማፂያኑ ቃል አቀባይ ሞሃመድ አብደልሳላም በበክኩላቸው ለአል ጃዚራ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፣ የእስራኤል መርከቦችን ወይም ወደ አካባቢው የሚያመሩ መርከቦችን ኢላማ ማድረጋቸውን እንደማያቆሙ አስታውቀዋል። ለአሜሪካ እና እንግሊዝ ጥቃትም አጸፋውን እንደሚመልሱ ዝተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG