በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሁቲ የጦር ቅኝት ጣቢያዎች ላይ ሌላ ዙር ጥቃት ፈጸመች


ከእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው ምስል ራፍ ታይፉን የተባሉት የጦር አውሮፕላኖች በየመን ኢላማዎችን ካደረሱ በኋላ በቆጵሮስ ራፍ አክሮቲሪ የጦር ሰፈር እንደተመለሱ ያሳያል ።
ከእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው ምስል ራፍ ታይፉን የተባሉት የጦር አውሮፕላኖች በየመን ኢላማዎችን ካደረሱ በኋላ በቆጵሮስ ራፍ አክሮቲሪ የጦር ሰፈር እንደተመለሱ ያሳያል ።

ሐሙስ አመሻሽ ላይ በተደረገ የመጀመሪያ ዙር የአየር ድብደባ የደረሰው ጉዳት አጥጋቢ እንዳልሆነ ባለስልጣናት መናገራቸውን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ የመን ውስጥ በሁቲ ኢላማዎች ላይ ዛሬ ማለዳ ሌላ ዙር ጥቃት ፈጽማለች ።

የዩኤስ ማዕከላዊ ዕዝ ተጨማሪውን ጥቃት ዩኤስኤስ ካርኒ ከተባለው እየተመራ ሚሳየሎችን ከሚያወድመው መርከብ ፣በባህር መጓጓዣ ፍሰቱ ላይ ቀጣይነት ያለው ስጋት ደቅኗል ባለው የቅኝት ጣቢያ ላይ በርካታ የቶማሃውክ ላንድ የጥቃት ሚሳኤሎችን መተኮሱን አስታውቋል ።

የአሁኑ ጥቃት የተፈጸመው የዩናይትድ ስቴትስ እና የእንግሊዝ ጦር በየመን የሁቲ ቦታዎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ከፈጸሙ ከአንድ ቀን በኋላ ነው ። ጥቃቶቹ በሁቲዎች ለተፈጸሙ ሳምንታትን ያስቆጠሩ፣ የባህር መጓጓዣን ያስተጓጎሉና በቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ-ሰላጤ ላይ እያለፉ የነበሩ መርከቦችን ላወደሙ ጥቃቶች አጸፋ መሆኑ ተነግሯል ።

የሁቲ ታጣቂዎች አርብ መጀመሪያ ላይ ፀረ- መርከብ ባሊስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፋቸውን የዩኤስ ወታደራዊ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል ። በጥቃቱ ምንም ዓይነት መርከብ አልተመታም።

የዩናይትድ ስቴትስ እና የብሪታንያ ባለስልጣናት ባለፈው ሐሙስ መገባደጃ ላይ የተጀመሩት እና አሁን ላይ ሁለት የጥቃት ማዕበሎች ተብለው የተገለጹት የመጀመሪያ ዙር ጥቃቶች ስኬታማ እንደሚሆኑ ያላቸውን ተስፋ በትናንትናው ዕለት ገልጸዋል።


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለስልጣን አርብ ዕለት ለቪኦኤ እንደተናገሩት የተደረገው የመጀመርያ ግምገማ ሐሙስ መገባደጃ ላይ የተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የጥቃት ማዕበል የሁቲዎችን ተጨማሪ ጥቃት የመክፈት አቅሙ መዳከሙን እንዳሳየ ተናግረዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG