በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሬክስ ቲለርሰን ለሩሲያ ጠንካራ መልዕክት አስተላለፉ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

ሩሲያ በጎረቤቶቿ ላይ በተለይ በምርጫ ሂደቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባች ምስቅልቅል ለመፍጠርና ኢ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን ለመጫን በተከታታይ ትከተለዋለች ያሉትን ባህርይዋን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አወገዙ።

ሩሲያ በጎረቤቶቿ ላይ በተለይ በምርጫ ሂደቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ እየገባች ምስቅልቅል ለመፍጠርና ኢ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን ለመጫን በተከታታይ ትከተለዋለች ያሉትን ባህርይዋን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አወገዙ።

በመጭው ሣምንት ወደ አውሮፓ የሚሄዱት ሚስተር ቲለርሰን ትናንት ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓ አጋሮቿ ድንበሮች የተጠበቁ እንዲሆኑና ከሩሲያ ነዳጅ እራሳቸውን ነፃ እንዲያወጡ እንደምታግዛቸው አመልክተዋል።

“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያንሠራራች ያለችው ሩሲያ የደቀነችውን ያፈጠጠ ሥጋት ዩናይትድ ስቴትስም አውሮፓም እንገነዘበዋለን” ብለዋል ሚስተር ቲለርሰን ትናንት፣ ማክሰኞ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ለተሰባሰቡ ታዳሚዎች ባደረጉት ንግግር።

ሬክስ ቲለርሰን ለሩሲያ ጠንካራ መልዕክት አስተላለፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

“ሩሲያ ባለፈው መስከረም በቦልቲክ ሃገሮች ወሰኖች አቅራቢያ ያደረገችው ‘ዛፓድ’ ወይም ‘ምዕራብ’ ብላ የሰየመችው የጦር ልምምድ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት የተቀናጀ እንቅስቃሴ የማድረጋችንን አስፈላጊነት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አጉልቶታል” ብለዋል ቲለርሰን።

ሩሲያ ቀደም ሲልም ጆርጅያና ዩክሬን ውስጥ ፈፅማቸዋለች ያሏቸውን ወረራዎች ያወገዙት አሜሪካዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃገራቸው ለአውሮፓ የምትመድበውን የመከላከያ በጀት እንደምታሳድግ አመልክተዋል።

ቲለርሰን አክለውም ዩክሬን ሙሉ ነፃነቷንና በመላ ግዛቷ ላይ ሉዓላዊነቷን መልሳ እስክትቀዳጅ ሩሲያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመጭው ሣምንት ውስጥ ብራስልስ ውስጥ በሚካሄደው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅቱ - ኔቶ እና ቪየና ላይ በተጠራው የአውሮፓቀ የፀጥታና የትብብር ድርጅት - ኦ.ኤስ.ሲ.ኢ. ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ከዋሺንግተን ከመነሣታቸው በፊት ያስተላለፏቸው መልዕክቶች እጅግ የጠነከሩ መሆናቸውን የሰሜን ካሮላይና ቻችል ሂል ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ተንታኝ ክላውስ ሌሬስ አመልክተዋል።

“ጥያቄው ‘ቲለርሰን ምን ያህል ተደማጭነት አላቸው?’ ነው፤ ‘የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ምን ያህል ጫና ማሳደር ይችላል?’ ነው። የውጭ ፖሊሲን በተመለከተ አዝማሚያውን የሚደግገው ፕሬዚዳንቱም ነው። ፕሬዚዳንት ትረምፕ ደግሞ አሜሪካ ለአውሮፓ በሚኖራት ቅርበትና ትስስር ጉዳይ ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት የተቀዛቀዘ ነው” ብለዋል ተንታኙ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይበልጥ የተነቃቃ በመሆኑ - ይላሉ ሌሬስ - የቲለርሰን ቃላት የአውሮፓ አጋሮችን ብዙም ላያረጋጋቸው ይችላል።

የምሥራቅ ዩክሬንን ሰላም አስመልክቶ (እአአ) በ2ዐ14 ዓ.ም. ሚንስክ ላይ ለተፈረመው ስምምነት ሩሲያ እንድትገዛ ዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ ግፊት ማሳደራቸው አግባብ ቢሆንም ክርም ልሣነ-ምድርን ለዩክሬን እንድትመልስ መወትወት ግን ፍሬ ላይኖረው እንደሚችል ክላውስ ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሬክስ ቲለርሰን ለሩሲያ ጠንካራ መልዕክት አስተላለፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG