በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ምርጫ ኒኪ ሄሊ ከውድድሩ እንደሚወጡ ይጠበቃል


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

ትናንት ማክሰኞ በተካሄደው “ሱፐር ቱስዴይ” የቅድመ ምርጫ ውጤት፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በየፓርቲያቸው ያላቸውን መሪነት ሲያጠናክሩ፣ የትረምፕ ተፎካካሪ የሆኑትና እጅግ አነስተኛ ድምፅ ያገኙት ኒኪ ሄሊ ከውድድሩ መውጣታቸውን ዛሬ ያስታውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባይደን ትናንት ምርጫ ከተደረገባቸው 15 ክፍለ ግዛቶች ውስጥ፣ በሰላማዊ ውቅያኖስ ከምትገኘው የአሜሪካ ግዛት ሳሞዋ ደሴት በስተቀር በሌሎቹ አሸንፈዋል።

የቀድሞ ፕሬዝደንት ትረምፕ በ14 ግዛቶች እንዳሸነፉ ሲታወቅ፣ የሪፐብሊካኑን ፓርቲ ለመወከል ሲፎካከሯቸው የሰነበቱት ኒኪ ሄሊ የቬርሞንት ክፍለ ግዛትን ብቻ አሸንፈዋል። ሄሊ ሁለት ግዛቶችን ብቻ ነው ያሸነፉት፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት በቅድመ ምርጫው ሳይቀናቸው ቢቀርም፣ “ትረምፕ መልሰው ሥልጣን ላይ የሚመጡ ከሆነ፣ ለአገራችን አይበጅም” በሚል ውድድራቸውን ቀጥለው ነበር።

በሥልጣን ላይ እንዳለ ፕሬዝደንት ከፓርቲያቸው ብዙም ተፎካካሪ የሌለባቸው ባይደን፣ በህዳር ወር ለሚደረገው ምርጫ ትረምፕን በድጋሚ ለመግጠም በዝግጅት ላይ ናቸው።

“ትረምፕ መልሰው ወደ ሥልጣን ከመጡ፣ ብጥብጥ፣ መከፋፈል፣ ጨለማ ይሰፍናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል ባይደን።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG