በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒኪ ሄሊ በኔቫዳ ሽንፈት ደረሰባቸው


ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከሁለቱ የሪፐብሊክን ፓርቲ እጩ ተፎካካሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት ኒኪ ሄሊ በስፓርታንበርግ ሳውዝ ካሎራይና እአአ ሰኞ የካቲት 5/2024
ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከሁለቱ የሪፐብሊክን ፓርቲ እጩ ተፎካካሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት ኒኪ ሄሊ በስፓርታንበርግ ሳውዝ ካሎራይና እአአ ሰኞ የካቲት 5/2024

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከሁለቱ የሪፐብሊክን ፓርቲ እጩ ተፎካካሪዎች መካከል አንዷ ኒኪ ሄሊ በኔቫዳ ክፍለ ግዛት ቅድመ ምርጫ ከባድ ሽንፈት ደርሶባቸዋል፡፡

የቅድመ ምርጫው ውጤት ለማሳያ ያህል እንጂ የማይመዘገብ ቢሆንም፣ የኔቫዳ የሪፐብሊካን ፓርቲ መራጮች “ከተፎካካሪዎቹ ማናቸውንም አንፈልግም ” የሚለውን አማራጭ በከፍተኛ ቁጥር የመረጡ ሲሆን ራሳቸውን በብቸኝነት ያቀረቡት ኒኪ ሄሊ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲን ፕሬዝዳንታዊ እጩነትን እየመሩ ያሉት የቀደሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እንዲሁ ለማሳያ በተካሄደው ቅድመ ምርጫ አልተሳፉም፡፡

ትረምፕ ያልተሳተፉት ከዚህ ግዛት ተወክለው በዋናው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች ስለማያስፈልጓቸው ነው፡፡

ይልቁን ትረምፕ ትኩረታቸውን ያደረጉት ፕሬዘዳንታዊ እጩውን ለመምረጥ የፊታችን ሀሙስ በሚደረግ የቡድን ውይይትና የድምጽ አሰጣጥ ላይ ሲሆን ይህ በይፋ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩነት እንዲቃረቡ ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡

ትናንት ማክሰኞ የታየው የኔቫዳው የምርጫ ውጤት በተፎካካሪዎቹ ውጤት ላይ ለውጥ የማያመጣ ቢሆን ከትረምፕ ጋር ለመወዳደር ራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ላቀረቡት ኒኪ ሄሊ አሳፋሪ ሆኖ ታይቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን የክፍለ ግዛቱን የዴሞክራቲክ ፓርቲው ቅድመ ምርጫ በቀላሉ አሸንፈዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG