በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክን የአሜሪካ ውጭ ጉዳዮ ሚኒስትር ሆኑ


አዲስ የተሾሙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
አዲስ የተሾሙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት በትናንትናው እለት፣ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እንዲመሩ ያጯቸውን አንተኒ ብሊንከንን ሹመት አጽድቋል፡፡

የአገሪቱ ዲፕሎማት ቁንጮ ሆነው የተሰየሙት ብሊንክን፣ በርካታ ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች እንደሚገጥማቸው ተነግሯል፡፡

“አሜሪካ ትቅደም” የሚለው የትራምፕ አስተዳደር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አቅጣጫ መቀየሩ በተነገረበት ሁኔታ ውስጥ፣ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎቹ ምክር ቤት፣ የብሊንከንን ሹመት 78 ለ 22 በሆነ ድምጽ አጽድቆላቸዋል፡፡

የአገሪቱ 71ኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ብሊንክን በተለይ ከዴሞክራቶቹ የምክር ቤት አባላት ብዙ ድጋፍ ተችሯቸዋል፡፡

የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት መሪ ሻክ ሹመር እንዲህ ብለዋል።

ብሊንክን የአሜሪካ ውጭ ጉዳዮ ሚኒስትር ሆኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00

“ብሊንከን በዓለም አቀፍ ደረጃ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት እንደገና ለመገንባትና ለማረጋገጥ የአሜሪካ ቀዳሚ ጉልበት የሆነውን ዲፕሎማሲ እንደ ለመመስረት ትክክለኛ ሰው ናቸው፡፡”

ብሊንከን በውጭ ጉዳይ ፖሊስ ረገድ በምክር ቤቱም ሆነ በፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር እንደ ምክትል ውጭ ጉዳዮ ሚኒስትር ሆነው ለአስርት ዓመታት ያገለገሉበት የሥራ ልምድ አላቸው፡፡

ይህን የሥራ ልምድ ግን አንዳንዶቹ የሪፐብሊካን አባላት፣ አሜሪካ ያንኑ የተለመደውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ብቻ ይዛ እንድትጓዝ የሚያደርግ ነው በማለት ይተቻሉ፡፡

በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን አባል ራንድ ፖል ከእነዚህ አንዱ ናቸው፡፡ እንዲ ብለዋል

"ብሊንከን ላለፉት 20 ዓመታት የዘለቀውን በመካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሲደግፉ የነበሩ ናቸው፡፡ አዲስ ፖሊሲ ይመጣልና ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ራሳችን ነው የምናሞኘው፡፡ የነበረው ነው የሚቀጥለው ፡፡"

የብሊንከንን ሹመት የደገፉት ሌላኛው ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል፣ ጂም ሪስች፣ ብሊንክን በኢራኑ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ያላቸውን አቋም ግን እንደሚቃወሙ እንዲህ በማለት አስታውቀዋል፡፡

“ከኢራን ጋር የተደረገውን አለም አቀፍ የኑክሌር ስምምነት መርሃ ግብር ለአሜሪካ ትልቅ ወድቀትና የውጭ ፖሊሲውንም ያበላሸ ነበር፡፡ ከብሊነክን ጋር ስነጋገር ይህን አመለካከት አይጋሩም፡፡ ለነገሩ አሁንም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ያንኑ ቀውስ ተሸክመው በመስራት ወደዚያው ወደነበረው ስምምነት ይመልሱናል፡፡”

ብሊነክን ባለፈው ሳምንት ለምክር ቤቱ አባላት ሲናገሩ አገራቸው ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን ተናግረው የሚከተለው አክለዋል፡፡

“ቻይናን መቅረብ ያለብን ከጥንካሬያችን ተነስተን ነው፡፡ ከድክመት አይደለም፡፡ መልካሙ ዜና ያንን የማድረግ አቅማችን በአብዛኛው በኛ ቁጥጥር ስር ነው፡፡ አብረን ስንሰራ ጥንክሬያች ነው፡፡ አጋሮቻችንን ማናናቅ የለብንም፡፡ የቻይናና ጉዳይ ስንስተናግድ የጥንካሬያችን ምንጭ የሚሆነውም ይህ ትብብር ነው፡፡”

ተንታኞች እንደሚሉት ብሊንከን ታምሶ የነበረውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገና ማቋቋሙም ሌላው ፈተና እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል፡፡ ከ'Center for American Progress' ከሚባለው ማዕከል ብራያን ከቱሊስ እንዲህ ይላሉ

“ከአራት ዓመታቱ የፖምፔዮ ቴለርሰን እና ትራምፕ አስተዳደር በኋላ የነበረው ሞራል እጅግ ቀዝቃዛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዲፕሎማቲክ ቡድን አባላት የሚሰማቸው ስሜት የቆየ ነው፡፡ ዲፕሎማቶቹ ፣ በአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) እና በሠራዊቱ ዘንድ የአሜሪካን የውጭ ዲፕሎማሲ በመወሰንም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮቹን በሚመለከት ረገድ፣ ለረጅም ጊዜ ከኋላ እንዲቀሩ መደረጋቸው ይሰማቸዋል፡፡”

ያለምንም ችግር በምክር ቤቱ የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች አልፈው ለሥልጣን የበቁት ብሊከን እነዚያን ፈተናዎች እንደሚጠብቋቸው ግን ተገምቷል፡፡ ዴሞክራቱ ሴንተር ባብ ማንዴዝ እንዲህ ይላሉ

“አርቆ አስተዋይ ናቸው፡፡ አገራችንን የገጠሟትን ውስብስብና ፈታኝ ፈተናዎችን ለመቋቋም፣ እንዲሁም ኮንግረስን በማሳተፍ ይሰራሉ፡፤ ከሁሉቱም ተቃራኒ ወገኖች ጋርም ያደርጉት እሱን ነው ፡፡”

ብሊንከን፤ ባለፈው ሳምንት ውስጥ፣ ሹመታቸው ከጸደቀላቸው የፕሬዚዳንት ባይደን የካቢኔ አባላት ጋር አራተኛው ሰው ናቸው፡፡

(ዘገባው የቪኦኤ ዘጋቢ የካትሪን ጊብሰን ነው)

XS
SM
MD
LG