በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ ኮሚቴ ስምምነት ደረሰ


Congressman Chris Smith
Congressman Chris Smith

የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድር ከዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ ጋር ለመቃኘት ያለመ ረቂቅ ህግ ዛሬ በህግ አርቃቂው የኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ ድምፅ እንዲሰጥበት ሙሉ በሙሉ ስምምነት ተደርሶበታል። /ከዚህ ጋር በተያያዘው የድምፅና የቪድዮ ዘገባ መግቢያ ላይ የሠፈረው መግቢያ ከዚህ ፅሁፍ ጋር በተያያዘው መሠረት እንዲስተካከል ከይቅርታ ጋር እየጠየቅን ከሙሉ ዘገባው የተሟላ መረጃ እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን/

የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድር ከዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ ጋር ለመቃኘት ያለመ ረቂቅ ህግ ዛሬ በህግ አርቃቂው የኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ ድምፅ እንዲሰጥበት ሙሉ በሙሉ ስምምነት ተደርሶበታል።

ለሙሉ ኮሚቴው ከቀረቡት ዘጠኝ የሕግ ረቂቆች አንዱ የሆነው ውሣኔ 128 የኒው ጀርሲው እንደራሴ ክሪስ ስሚት እና ከሃምሣ በላይ የኮንግረስ አባላት የደገፉት ነው።

የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት እንደራሴው ክሪስ ስሚዝ ባሰሙት ቃል “ኢትዮጵያ ጠቃሚ ወዳጅና በዓለም አቀፍ ሰላም ጥበቃ ውስጥም አጋር ብትሆንም እየቀጠሉ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ፈፅሞ ተቀባይነት የላቸው” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ ኮሚቴ ውሣኔ አሣለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

“በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙ የዘፈቀደ እሥራቶች፣ ግድያዎችና የማሰቃየት አድራጎቶች፣ በመናገርና በመደራጀት ነፃነቶች ላይ እየተጣሉ ያሉ እገዳዎች፣ በተቃዋሚዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚካሄዱ በፖለቲካው የሚመሩ የፍርድ ሂደቶች፣ የማዋከብና የማሸማቀቅ ድርጊቶች .... ሪፖርቱን ስታነብቡት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የቀረበ ክሥ ዓይነት ነው” ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለው።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ፋይሎች ይክፈቱ

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ ኮሚቴ ውሣኔ አሣለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG