በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የአስቸኩዋይ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ይጨምራል ተባለ


በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ፓትሪሻ ሃስላክ
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ፓትሪሻ ሃስላክ

በኢትዮጵያ እንደሚጨምር ከሚጠበቀዉ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር አንጻር ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች፣ ሌሎች አጋሮች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸዉን አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ በዚህ እየተጠናቀቀ ባለዉ የአዉሮፓዉን 2015 ዓም አገራቸዉ ለኢትዮጵያዉያን የ128 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረግዋን ተናግረዋል። ለኢትዮጵያ (Safety Net) ፕሮግራምም አገራቸዉ በያመቱ 100 ሚሊዮን ዶላር እየሰጠች መሆኑን ጨምረዉ ገልጸዋል።

(HRD) የሚባለዉ የሰብአዊ እርዳታ ሰነድ የፊታችን ታህሣሥ ወር በኢትዮጵያ መንግስት ይፋ ሲደረግ፣ የአስቸኩይ ጊዜ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን እንደሚያንጸባርቅ እንጠብቃለን ብለዋል። በዓለም ዙሪያ ሌሎች የእርዳታ ፍላጎቶች ስላሉ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር በጊዜ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የአዲስ አበባ ዘጋቢአችን እስክንድር ፍሬዉ ከአምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ ጋር ያደረገዉን ቃለ ምልልስ መሰረት በማድረግ ያጠናቀረዉን ዘገባ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

በኢትዮጵያ የአስቸኩዋይ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ይጨምራል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00

XS
SM
MD
LG