በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ጉዳይ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሞስኮ የተያዙ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች


የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን

በሩሲያ እና ዩክሬን ድንበር ላይ ያለው የግጭት ሥጋት ዛሬ በሞስኮ እና በዋሽንግተን በተናጠል የተካሄዱ ንግግሮች ዋናው የትኩረት አጀንዳዎች ነበሩ።

ሞስኮ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ተገናኝተው ሲነጋገሩ፤ በዋይት ኃውስ ደግሞ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጀርመኑን መራሄ መንግሥት ቻንስለር ኦላፍ ሹልስን ተቀብለዋል።

ከዋይት ኃውስ የተገኘ ዜና እንዳመከተው ባይደን እና ማክሮን ትናንት እሁድ በስልክ መነጋገራቸውን እና ሩሲያ በዩክሬን ድንበሮች ላይ የከሰተችውን ወታደራዊ ፍጥጫ ለማምከን በታለሙ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እና እንዲሁም የዩክሬንን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት አስመልክቶ ያላቸውን ድጋፍ ማረጋገጣቸውን አመልክቷል።

ማክሮን ባለፈው ሳምንት በሰጡት አስተያየት ቅድሚያ የሚሰጡት "ከሩሲያ ጋር ለሚደረጉ ንግግሮች እና እየተባባሰ ያለውን ሁኔታ ማርገብ ለሚያስችሉ ጉዳዮች ነው” ብለው ነበር።

የጀርመኑም ቻንስለር በመጭው ሳምንት ወደ ሞስኮ እና ኪየቭ ተመሳሳይ ጉዞዎችን ለማድረግ ዕቅድ ይዘዋል።

ግጭቱን ለማስቀረት የተያዙት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተካሄዱ ያሉት “ሩስያ በዩክሬይን ላይ የምትፈጽመው ወረራ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል" የሚለውን ማስጠነቀቂያ ዩናይትድ ስቴትስ እያሰማች ባለበት ወቅት ነው።

የዩናይትድ ስቴትሱ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ሱሊቫን ትላንት እሁድ ለኤንቢሲ ቴሌቭዥን ጣቢያ ‘MEET THE PRESS’ ለተሰኘው ፕሮግራም በሰጡት አስተያየት ነበር ይህን ያሉት ።

ሱሊቫን ከፎክስ ኒውስ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ሌላ ቃለምልልስ "ሩሲያ በማንኛውም ሰዓት በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ ወይም በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ሞስኮ 70 በመቶ የሚሆነውን አጥቂ ኃይሏን ማዘጋጀቷን የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ባለሥልጣናት ግምገማ ጠቅሰው ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG