በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ - ዩክሬን - ዋሺንግተን

This handout satellite image released by Maxar Technologies shows a close up of armored personnel carriers and trucks at Russia's Klimovo storage facility, in Bryansk Oblast, 13 kilometers north of the Russia/Ukraine border, Jan. 19, 2022.

ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ልታሠፍር ከምትፈልገው ተዋጊ ኃይል በዚህ የአውሮፓ ወር አጋማሽ ሰባ ከመቶውን እንደምታስገባና ቦታ እንደምታስይዝ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ይህ ጠንካራ አቅም ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ ለመክፈት እንደሚያስችላቸው ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

“ማንነታቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ” ሲል አሶሽየትድ ፕሬስ የጠቀሳቸው እነዚህ ባለሥልጣናት የውስጥ ክትትል ማካሄዳቸውንና ፑቲን በመጭዎቹ ጥቂት ሣምንታት ውስጥ ሊወርሩ እንደሚችሉ ቢናገሩም ዲፕሎማሲያዊ መፍትኄ ለማፈላለግ አሁንም ዕድል እንዳለ ገልፀዋል።

ተዋጊ ጦር ወደ ዩክሬን እንደማያዘምቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በተደጋጋሚ ያሳወቁ ቢሆንም ‘የኔቶን ምሥራቃዊ መከላከያ ለማጠናከር’ በሚል ወደ ፖላንድና ወደ ሮማንያ የጠቅላይ ዕዝ ሠራተኞችንና ተዋጊ ወታደሮችን መላካቸው ተዘግቧል።

“ዩናይትድ ስቴትስ መሠረተ-ቢስ ፍርሃት እየነዛች ነው” የምትለው መስኮብ ዩክሬንን የመውረር ዕቅድ እንደሌላት እየተናገረች ነው።

XS
SM
MD
LG