በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን አስተዳደር በቻይና ኦሎሚክ የዲፕሎማሲ እቀባ በማድረግ አይሳተፍም


ዩናይትድ ስቴትስ የባይደን አስተዳደር እኤአ በ2022 በሚደረገው የቤጂኒግ የክረምት ኦሎምፒክ ላይ የዲፕሎማሲ እቀብ በማድረግ ከዩናይትድ ስቴትስ አትሌቶች ውጭ ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን እንደማይሳተፍ አስታወቀ፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ትናንት ለጋዜጠኞች እንዳደረጋገጡት ዩናይትድ ስቴትስ ማንኛውንም የዲፕሎማት ተወካይ ወይም ባለሥልጣን ወደ ቻይናው የክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታዎች አትልክም ብለዋል፡፡

ይህ መሆኑም በቻይና ዚንጂያንግ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ዘር ማጥፋትና በሌሎች የሰአብዊ ጥቃቶች የተነሳ በመሆኑ እንደሆነ ቃል አቀባይዋ ገልጸዋል፡፡

“በዩናይትድ ሴቴትስ ቡድን ውስጥ ያሉ አትሌቶች ሙሉ ድጋፋችን አላቸው” ያሉት ጄን ሣኪ “መቶ በመቶ ከኋላቸው ነን ከዚህ ሆነን ድጋፋችንን እንገልጽላቸዋልን” ብለዋል፡፡

አትሌቶቹን ሳይጨምር የዲፕሎማሲው መገለል የተወሰነው እኤአ በ1980 በፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ዘመን ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን ወራለች በሚል ዩናይትድ ስቴትስ አትሌቶችዋን ከሞስኮው የበጋ ኦሎሞፒክ በማገድ የፈጸመችውን ስህተት ላለመድገም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቻይና በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሙስሊም ቻይናውያንን አስራለች፣ በሆንግ ኮንጎ የዲሞክራሲ ኃይሎችን ታጠቃለች የሚለውን ጨምሮ፣ ትፈጽማዋለች በሚባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ፕሬዚዳንት ባይደን እርምጃዎችን እንዲወስዱ፣ በህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ ግፊት እየደረሰባቸው መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ከዋይት ሀውሱ መግለጫ በፊት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዛሆ ሊሃን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እምርጃውን የምትወስድ ከሆነ ቻይና አጸፈውን እንድምትወስድ አስጠንቅቀው ነበር፡፡፡፡

ባይደን ባለፈው ወር እኤአ የካቲት 4 እስከ 20 በሚደረገው የቻይናው የክረምት ኦሎምፒክ የዲፕሎማሲ ተአቅቦ እንደሚያደርጉ አስታውቀው ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG