በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስደተኞች - የመንግሥታት ‘መናገጃ ሸቀጥ’

ፎቶ ፋይል፡- የሮሂንጃ ሙስሊሞች
ፎቶ ፋይል፡- የሮሂንጃ ሙስሊሞች

ለአካባቢያዊና ብሔራዊ ጥቅሞቻቸው ሲሉ መንግሥታት የፖለቲካ ጨዋታቸውን ለማጋጋል ስደተሆናችን መጠቀሚያ እያደረጉ በሄዱ መጠን ከጦርነትና ከመሳደድ እየሸሹ ለሚወጡ ሰዎች የሚሰጠው ጥገኝነትና ከለላ እየተሸረሸረ እየተሸረሸረ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አስጠነቀቁ።

ባለፈው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ በዓለም ዙሪያ 65.6 ሚሊየን ሰው በኃይል መፈናቀሉን ከፍተኛ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

ይህ ብዛቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ሰው በኃይል የተፈናቀለው በጦርነቶችና በሚደርስባቸው ማሳደድ ምክንያት እንደሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቆ “ከተፈናቀሉት 22.5 ሚሊየን የሚሆኑት ድንበር እያሳበሩ ከየሃገሮቻቸው ወጥተዋል” ይላል።

በዚህ ዓመት ብቻ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሰው ከየሃገሩ ተሰድዷል።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየውን ዓለምአቀፍ ሁኔታ አስመልክቶ የዩኤንኤችሲአር ኃላፊ በትካዜ ስሜት ባደረጉት ንግግር ባለፉት አምስት ሣምንታት ውስጥ ብቻ ግማሽ ማሊየን የሚሆኑ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ሚያንማር ውስጥ ‘እየተካሄዱባቸው ናቸው’ ካሉት ዘግናኝ ጥቃቶች ለማምለጥ ተሰድደዋል።

በእነዚሁ ሣምንታት ውስጥ ሃምሣ ሺህ ከደቡብ ሱዳን፣ 18 ሺህ ደግሞ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እየተፈናቀሉ ወጥተዋል።

ሁኔታው በሌሎች አካባቢዎችም የዚያኑ ያህል የከፋ መሆኑን ግራንዲ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የስደተኞች - የመንግሥታት ‘መናገጃ ሸቀጥ’
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG