በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወቅቱ የአዳጊ ሃገሮች ግብ በ 15 አመታ ውስጥ ድህነትን ማጥፋት እብደሆነ ተገለጸ


ዛሬ በአለማችን የሚገኙት የመጨረሻዎቹ አዳጊ ሀገሮች ለሚቀጥሉት 15 አመታት ድህነትን ከምድረ-ገጽ ፈጽሞ ለማጥፋት በሚደረገው ፍልሚያ ወሳኝ የትግሉ መድረክ እንደሚሆኑ ተገለጸ።

ዛሬ በአለማችን የሚገኙት የመጨረሻዎቹ አዳጊ ሀገሮች ለሚቀጥሉት 15 አመታት ድህነትን ከምድረ-ገጽ ፈጽሞ ለማጥፋት በሚደረገው ፍልሚያ ወሳኝ የትግሉ መድረክ እንደሚሆኑ ተገለጸ። ሽንፈቱም ሆነ ድሉ የሚታየውም በነዚህ ሀገሮች እንደሚሆነ ተገለጿል።

“በሚለንየሙ የልማት ግቦች ሁሉም የድህነት መገለጫዎችን በተወሰነ መጠን መቀነስ ነበር። ለምሳሌ እአአ ከ 1990 እስከ 2015 አም ባሉት አመታት ውስጥ ድህነትን በግማሽ መቀነስ የህጻናትን ሞት ደግሞ በሁለት ሶስተኛ መቀነስ የመሳሰሉት ነበሩ። አሁን ግን በዚህ በተያዘው የተከታታይ የልማት ግቦች ድህነትን ፈጽሞ ማጥፋት ወይንም ማስወገድ ነው። ወይም የህጻናትን ሞት ሊያስከትሉ የሚችሉ በሽታዎችን ማስወገድ ነው። እና ግቦቹን በተመለከተ እጅግ ከፍ ያለ ኢላማ ተቀምጧል። ታድያ ከፍ ያለ ኢላማ ሲቀመጥ ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ተመጣጣኝ ፕሊሲዎችን መንደፍና ምላሽ መስጠትም ያስፈልጋል”

“ስለሆነም ተከታታይ የልማት ግቦችን ለመምታት ፈተናው የሚበዛውና ዋናው ፍልሚያው የሚካሄደው በመጨረሻዎቹ አዳጊ ሀገሮች ውስጥ በተለይም በገጠር ቀበሌዎች ይሆናል። በተጨማሪም የመሰረተ-ልማቶች ክፍተት የሚታየውና ተጨማሪ የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት የሚያስፈልገውም እዚ ላይ ነው። ለምሳሌ በገጠር የሚገኘው የድህነት መጠን በከተማ ከሚገኘው በእጥፍ ይጨምራል። በሌላ በኩል ግን መገንዘብ የሚያስፈልገው ከነዚህ አዳጊ ሃገሮች ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ፣ ታንዜንያና ኡጋንዳን የመሳስሉ ጥቂት ሀገሮች በገጠር ድህነትን ለመቀነስ ከፍ ያለ ስራ አከናውነዋል።”

"እናም ስለአንድ ብሄራዊ የምጣኔ ሀብት ልማት ስንነጋገር ዋናው ቁም ነገር በገጠሩና በከተማው ልማት መካከል ስላለው ሚዛን ነው። ነገር ግን በከተማው ውስጥም የግብርናውን ዘርፍ ከፍ ማድረግና ምርታማነትን በመጨመር እንዲሁም ከዛ ውጭ ባለው የኢኮኖሚ ዘርፍ መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ ይጠይቃል። የዚያን ጊዜ ነው ትክክለኛ የመዋቅር ለውጥ ማግኘት የሚቻለው። የዚህ ዘገባ መልእክትም ይኸው ነው።”

ከላይ የተጠቀሱትን የባለሞያ ዶ/ር ጌታቸውን ቃለ ምልልስ፣ የአዲስ አበባው ዘጋብያችን መለስካቸው አመሃ ዝርዝር ልኮልናል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የወቅቱ የአዳጊ ሃገሮች ግብ በ 15 አመታ ውስጥ ድህነትን ማጥፋት እብደሆነ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:42 0:00

XS
SM
MD
LG