ዋሺንግተን ዲሲ —
አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣን በሶሪያ ራካ ከተማ ውስጥ “እሥላማዊ መንግሥት” በተባለው ነውጠኛ ቡድን የታገቱ 20 ሺህ ዜጎች ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አስጠነቀቁ፡፡
ከዚህ አደጋ እንዲያመልጡም የሚቻለው ሁሉ መደረግ አለበት ብለዋል ባለሥልጣኑ፡፡
በሶርያ ጉዳይ ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ዋና አማካሪ ኢያን ኤግላንድ በራካ የተለያዩ መንደሮች በእስላማዊ ግዛት ታግተው የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ