በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን 18 ሚሊዮን ህዝብ ከባድ የምግብ ዕጥረት ቀውስ ተደቅኖበታል


ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን በተፈጠረው ግጭት ተፈናቀሉ በገዳረፍ በጎ አድራጎት ድርጅት እርዳታ ለመቀበል እየተጠባበቁ ገዳረፍ፣ ሱዳን፣ እአአ 30/2023
ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን በተፈጠረው ግጭት ተፈናቀሉ በገዳረፍ በጎ አድራጎት ድርጅት እርዳታ ለመቀበል እየተጠባበቁ ገዳረፍ፣ ሱዳን፣ እአአ 30/2023

የእርስ በርስ ጦርነቱ አንድ ዓመት ሊደፍን በተቃረበባት በሱዳን 18 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ እጅግ የከበደ የምግብ ዋስትና እጥረት ቀውስ የተጋረጠበት መሆኑን አስታወቁ፡፡ የሰብዓዊ ረድዔት ባለስልጣናት ትናንት ረቡዕ ለተ መ ድ የጸጥታ ምክር ቤት ባደረጉት ገለጻ በተለይ በብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን ባለስልጣናቱ አሳውቀዋል፡፡

ቁጥራቸው ወደ 730 ሺህ የሚጠጋ ህጻናት ለከባድ የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት እንደሚጋለጡ የተናገሩት ባለስልጣናቱ 240 ሺሁ ከባድ ውጊያ የሚካሄድበት የዳርፉር ክፍለ ግዛት ሕጻናት መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በአንዳንዱ የሱዳን አካባቢ 5 ሚሊዮን ሰዎች ከለየለት የረሃብ ቸነፈር መለስ ለሚል ረሃብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የተ መ ድ አስጠንቅቋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ሞሪዚዮ ማርቲና ሲናገሩ ጦርነቱ የረሃቡን ሁኔታ እያባባሰው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG