በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የሱዳን ተፋላሚዎች በሲቪሎች ላይ ወንጀል ፈጽመዋል አለ


የሱዳን ስደተኞች በቻድ ድንበር
የሱዳን ስደተኞች በቻድ ድንበር

ተ.መ.ድ በሱዳን በውጊያ ላይ የሚገኙትን ሁለቱንም ተቀናቃኞች ሃይሎች በሲቪሎች ላይ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ሲል ወንጀለ። የመንግስታቱ ድርጅት “አንዳንዶቹ ጥሰቶች በአለም አቀፍ ህግ ጥሰት እንደጦር ወንጀሎች መታየት ይገባቸዋል” ሲል አስታውቋል።

ድርጅቱ ከጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዚያ 15 እስከ ታህሳስ 2023 ማብቂያ ባለው ጊዜ ውስጥ 303 ተጎጅዎችን እና ምስክሮችን አነጋሮ፣ የቪዲዮ፣ የምስል እና የሳተላይት ምስሎችን አሰባስቦ የ16 ገጽ ሪፖርት አጠናቅሯል።

ሪፖርቱ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች እና የመንግስት ሃይሎች ለ 14,600 ሰዎች ህልፈት እና በትንሹ ለስምንት ሚሊየን ሰዎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ስደት መንስዔ ሆነዋል ሲል አስታውቋል።

ሪፖርቱ በተጨማሪም በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 15/2023 118 ሰዎች ላይ የቡድን አስገድዶ መድፈር ሙከራን ጨምሮ አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

የመንግስታቱ ድርጅት የቀጠናው የሰብዓዊ መብት ቃል አቀባይ ተቀናቃኞቹ ንብረት ዘርፈዋል፣ ህጻናት ወታደሮችን መልምለዋል፣ እንዲሁም የችግረኛ እና የአቅመ ቢስ ሰዎችን መብት ረግጠዋል ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም በኬኒያ ናይሮቢ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ በብሄራቸው እና ፈጥኖ ደራሽ ቡድኑን ደግፈዋል በሚል ግምት የተገደሉ ተማሪዎችም አሉ ብለዋል።

ማጋንጎ ‘መሳሪያዎች ቆመው ዜጎች ደህነታቸው ሊጠበቅ ይገባል’ ሲሉ አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG