በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭቶችና በተፈጥሮ ችግር ውስጥ ያሉ ሕዝቦች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚፈልጉ የተመድ አስታወቀ


የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበራ ቢሮ(OCHA) ባወጣው የ2016 ዓ.ም ዝርዝር ሪፖርት፣ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ አመልክቶ፣ የእርዳታ ፈላጊው ሕዝብ ቁጥር ወደ 130 ሚልዮን አሻቅቧል ሲል ገልጧል። ይህም ካለፈው ዓመታዊ ሪፖርት ጋር ሲተያይ በ44 ሚሊዮን የበለጠ ነው።

በተጨማሪም የሚፈለገው የእርዳታ መጠን በ$2 ሚሊዮን ጨምሮ ወደ $21.6 ቢልዮን አድጓል። አሁን ገቢ የሆነው ደግሞ $5.5 ቢልዮን ብቻ መሆኑ ተገልጧል።

«ለሰብዓዊ እርዳታ ከሚለገሰው ገንዘብ ውስጥ 80 ከመቶ የሚሄደው፣ በግጭቶች ምክንያት ወደተጎዱ ወገኖች ነው» ሲሉ፣ ጀነስ ላረከ የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበራ ቢሮ ቃል-አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

“እነዚህ በየቦታው ተሰበጣጥረው፣ ለምሳሌም በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ፣ በሦርያ፣ በደቡብ ሱዳን የሚታዩ ግጭቶች፣ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ናቸው። እርዳታ ፈላጊዎቹ ብዛት ስላላቸው ብቻም አይደለም፣ ቦታዎቹ አስቸጋሪና ለደኅንነትም አስተማማኝ ያለመሆቸው ጭምር እንጂ!”

በዓለማችን የሚገኙ ያልተጠበቁና የግዳጅ ተፈናቃዮችም፣ የእርዳታ አቅርቦቱ ዘለግ እንዲልና የበጎ አድራጊዎቹም ቁጥር እንዲጨምር አስገድደዋል። አንድ በቅርቡ ይፋ የሆነ የተመድ የስደተኞች መሥሪያ ቤት ዘገባ እንዳመለከተው፣ 65 ሚሊዮን ከአለም ሕዝብ ስደተኞች አልያም የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው። የተፈጥሮ-ሰራሽ አደጋ ሰለባዎችም፣ የዓለማቀፍ በጎ-አድራጊዎችን እጅ የሚጠብቁ መሆናቸውን፣ የተመድ አመልክቷል።

ኢትዮጵያና ዚምባብዌ ውስጥም፣ ኤል-ኒኞ፣ ከፍተኛ ድርቅ አስከትሎ፣ ሰብል ጠፍቷል፥ ከፍተኛ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይ ያድምጡ።

በግጭቶችና በተፈጥሮ ችግር ውስጥ ያሉ ሕዝቦች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚፈልጉ የተመድ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG