የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ማስተባበራ ቢሮ(OCHA) ባወጣው የ2016 ዓ.ም ዝርዝር ሪፖርት፣ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ አመልክቶ፣ የእርዳታ ፈላጊው ሕዝብ ቁጥር ወደ 130 ሚልዮን አሻቅቧል ሲል ገልጧል። ይህም ካለፈው ዓመታዊ ሪፖርት ጋር ሲተያይ በ44 ሚሊዮን የበለጠ ነው።
በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኰሚሽነር ዛይድ ራዓድ አል-ሁሴን ገለጻ መሠረት፣ በመላው ዓለም የሰብዓዊ መብት እሴቶችና ነፃነቶች አደጋ ላይ ናቸው። ኰሚሸሩ ይህን ያስታወቁት፣ በተመድ 32ኛው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር ነው።