በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ የተኩስ ማቆም እንዲደረግ ተመድ ወሰነ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሐማስ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረገ በከፍተኛ ድምፅ ወስኗል፤ ኒው ዮርክ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሐማስ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረገ በከፍተኛ ድምፅ ወስኗል፤ ኒው ዮርክ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሐማስ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረገ በከፍተኛ ድምፅ ወስኗል። የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት እንዲቆም ዓለም ድጋፉን ያሳየበት መድረክ ነው ተብሏል። የውሳኔ ሐሳቡ አሜሪካ እና እስራኤል እየተገለሉ መምጣታቸውንም ያምላከተ እንደሆነ ተነግሯል።

ከ193 ዓባል አገራት ውስጥ 153 ውሳኔውን ሲደግፉ፣ 10 ተቃውመዋል። 23 ደግሞ በድምጸ ተአቅቦ አልፈውታል። ሆኖም ግን የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ፣ እንደ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የሕግ አስገዳጅነት የለውም። የፀጥታው ም/ቤት ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሃሳብ ሊያስተላልፍ ሞክሮ፣ አሜሪካ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ አድርጋለች፡፡

በተመድ የፍልስጤማውያን አምባሳደር ሪያድ ማንሱር ከድምፅ አሰጣጡ በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ ጠቅላላ ጉባኤው ክብደት ያለው መልዕክት ያስተላለፈበት ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።

“በሕዝባችን ላይ የተቃጣውን ወረራ የማስቆም እና ሕይወትን የመታደግ የጋራ ኃላፊነት አለብን” ብለዋል ማንሱር።

ለእስራኤል ዋና የጦር መሣሪያ ምንጭ እና አጋር የሆነችው አሜሪካ፣ እስራኤል ጦርነቱን እንድታቆም ልታሳምናት የምትችል ብቸኛ አገር ተደርጋ እንደምትታይ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG