በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ለእስራኤል-ሐማስ የተኩስ አቁም ጥሪ ድምፅ ይሰጣል


በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ በጥቃቱ የፈራረሰው የፍልስጤም ቤቶች
በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ በጥቃቱ የፈራረሰው የፍልስጤም ቤቶች

በጋዛ አፋጣኝ የሰብዓዊነት ተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚጠይቀው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ለመወያየት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ማክሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል።

በመንግሥታቱ ድርጅት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ "በጋዛ ሰርጥ ያለው አስከፊ ሰብአዊ ሁኔታ እና የፍልስጤም ሲቭል ማኅበረሰብ ስቃይ" አሳሳቢ መሆኑን ይገልፃል። ሁሉም ወገኖች የዓለም አቀፍ ህጉን እንዲያከብሩ፣ ታጋቾችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና ሰብአዊ ተደራሽነትን እንዲያረጋግጡም ጥሪ አቅርቧል።

ባለፈው ሳምንት በፀጥታው ምክርቤት ቀርቦ የነበረው ተመሳሳይ የውሳኔ ሀሳብ፣ አሜሪካ ድምፀ ተዓቅቦ በማድረጓ ምክንያት ከሽፏል። በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሚያልፉ ውሳኔዎች በህግ አስገዳጅ ባይሆኑም፣ ፖለቲካዊ ክብደት ግን ይኖራቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ሰኞ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በፀጥታው ምክር ቤት የቀረበውን ውሳኔ ሀሳብ ለምን እንደተቃወመች አስረድተዋል። "ለሰብዓዊ አቅርቦት ጊዜያዊ ተኩስ ማቆምን እንደምንደግፍ ግልፅ አድርገናል" ያሉት ሚለር "እ.አ.አ ጥቅምት 7 የተካሄደውን ጥቃት ያሴረው የሐማስ አመራር በጋዛ እንዲቀጥል እና የወደፊት ጥቃቶችን እንዲያቅድ የሚፈቅድ የተኩስ አቁም ስምምነት ግን ተቀባይነት የሌለው ነው" ብለዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ድምፅ ለመስጠት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ በጋዛ የሚካሄደው ውጊያ የቀጠለ ሲሆን፣ እስራኤል በመካከለኛው እና በደቡብ ጋዛ የአየር ጥቃቶችን አካሂዳለች።

እስራኤል በምትቆጣጠረው ዌስት ባንክ ውስጥ የሚገኘው የፍልስጤም ጤና ሚኒስትር በበኩሉ እስራኤላውያን ጄኒን በተሰኘች ከተማ ባደረሱት ጥቃት አራት ፍልስጤማውያንን መግደላቸውን አስታውቋል። ሐማስ በእስራኤል ላይ ካደረሰው ጥቃት ወዲህ 270 የሚደርሱ ፍልስጤማውያን በዌስት ባንክ ተገድለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG