በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከስምምነቱ በኋላም “ጥሰቶች ቀጥለዋል” - የተመድ ኮሚሽን


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የሰላም ሥምምነት ከተፈረመ ከአንድ ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ የጦርና በሰብዕና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቀጥለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሙያዎች ቡድን ዛሬ፣ ሰኞ አስታውቋል።

ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና ባለፈው ኅዳር በቆመው ጦርነት በሺሆች የሚቆጠሩ መገደላቸውን፣ በሁለቱም በኩል ያሉ ወገኖች መደዳ ግድያ፣ መድፈር እና በዘፈቀደ ማሰርን ጨምሮ ጭካኔ የተሞላባቸው ወንጀሎችን በመፈፀም ሲወነጃጀሉ መቆየታቸውንና ለተፈፀሙት የመብቶች ጥሰቶች ማናቸውም ኃላፊነት አለመውሰዳቸውን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል።

ይህንኑ ጉዳይ እንዲመረምር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ባለሙያዎች ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ ቻንዴ ኦትማን ከሪፖርቱ ጋር ያወጡትን መግለጫ ሮይተርስ ሲጠቅስ "ስምምነቱ በአብዛኛው ተኩስ እንዲቆም ቢያደግም በሃገሪቱ ሰሜን፣ በተለይ በትግራይ ለግጭቱ መፍትኄ ማስገኘትና አጠቃላይ ሰላም ማስፈን አልቻሉም” ማለታቸውን ገልጿል።

“በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ መሆኑን” ሊቀመንበሩ መናገራቸውንና ኮሚሽኑ በሪፖርቱ “ትግራይ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአሳሳቢ ሁኔታ ቀጥሏል” ማለታቸውን፤ “የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደሚፈፅም” ማስፈሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አሁንም ከጦር ወንጀል የሚተካከሉ ጥቃቶች እንደቀጠሉ የተመድ ቡድን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:26 0:00

የእነዚህ ኃይሎች አባላት በግድያ፣ በማሰቃየት፣ በመድፈርና ተመጣጣኝ በሆነ ፆታዊ ጥቃት፣ ወሲባዊ ባርነት፣ ሰውን በባርነት መያዝና በማሰር ወይም በሌሎች የከበዱ ነፃነቶችን የመግፈፍ አድራጎቶች ወንጀሎችን ፈፅመዋል”

ሪፖርቱ “በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ከክልል ልዩ ኃይሎች ትግራይ ክልል ውስጥ መጠነ ሰፊና የተቀናጀ ጥቃት ሲቪሎች ፈፅመዋል” ያለው የኮሚሽኑ ሪፖርት “የእነዚህ ኃይሎች አባላት በግድያ፣ በማሰቃየት፣ በመድፈርና ተመጣጣኝ በሆነ ፆታዊ ጥቃት፣ ወሲባዊ ባርነት፣ ሰውን በባርነት መያዝና በማሰር ወይም በሌሎች የከበዱ ነፃነቶችን የመግፈፍ አድራጎቶች ወንጀሎችን ፈፅመዋል” እንደሚል ዘገባው ይናገራል።

የኢትዮጵያ መንግሥትና የጦር ኃይሎቹ በግልም ሆነ ከኤርትራ ኃይሎች ጋር ሆነው የሚባሉትን ወንጀሎች አለመፈፀማቸውን እየተናገሩ ክሦቹን በተደጋጋሚ ማስተባበላቸውን፣ መንግሥቱ በቀረቡት የተናጠል አቤቱታዎች ላይ ምርመራዎችን እንደሚያካሂድ ቃል መግባቱን፣ የአማራ ክልል ባለሥልጣናትም ኃይሎቻቸው ትግራይ ውስጥ የጭካኔ አድራጎቶችን አለመፈፀማቸውን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG