በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀጥታው ምክርቤት በኮንጎ አለመረጋጋት በማባባስ ስድስት ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ውድ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ውድ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ በዚህ ዓመት ግጭት እየጨመረ በሄደባት ኮንጎ ውስጥ አለመረጋጋትን የሚያባብሱ እንቅስቃሴዎችን በማካሄድ እና የሰብዓዊ ቀውሱን በማባባስ አስተዋፅኦ አድርገዋል ባላቸው ስድስት ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።

ምክርቤቱ ማዕቀብ የጣለባቸው ግለሰቦች የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጀነራል፣ የተባባሩት ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች የተሰኘው የዩጋንዳ ታጣቂ ቡድን ሁለት ከፍተኛ መሪዎች፣ በሩዋንዳ የሚደገፈው የኤም-23 ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ፣ የሕዝቦች ብሔራዊ ጥምረት ለኮንጎ ሉዓላዊነት የተሰኘው ቡድን መሪ እና፣ ትዊርዋኔሆ የተሰኘው የኮንጎ ታጣቂ ቡድን ኮማንደር ናቸው።

ማዕቀቡ የተጣለው ምክርቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሲሆን፣ ሩዋንዳም በኮንጎ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት እያባባሰች እንደሆነ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ውድ ተናግረዋል።

የፀጥታው ምክርቤት በኮንጎ አለመረጋጋት በማባባስ ስድስት ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጣለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:56 0:00

"ሩዋንዳ ለኤም-23 የምትሰጠውን ድጋፍ ማቆም አለባት" ያሉት ውድ በተጨማሪም የሩዋንዳን ኃይሎች ኮንጎ ግዛት ማስወጣት እና፣ የመንግስታቱ ድርጅት ኮንጎን ለማረጋጋት ባቋቋመው የተልዕኮ ቡድን (ሞኑስኮ) ላይ ሆን ተብሎ መተኮሱን በታማኝ ሪፖርት የተረጋገጠውን ማንኛውንም ከመሬት ወደ ሰማይ ተወንጫፊ የሚሳይል ስርዓት በአስቸኳይ እንድታስወግድም ጠይቀዋል።

ውድ አክለው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ጦርነት ለማስቆም እና በኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል። በኮንጎ እየተባባሰ ለሄደው አለመረጋጋት ኮንጎ እና ሩዋንዳ እርስበርስ ይወነጃጀላሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማክሰኞ እለት በግጭቱ ምክንያት ለሰብዓዊ ቀውስ ተጋላጭ የሆኑ ዘጠኝ ሚሊየን ሰዎች ለመርዳት 2.6 ቢሊየን ዶላር የጠየቀ ሲሆን፣ በኮንጎ በአጠቃላይ 25 ሚሊየን ሰዎች ርዳታ ጠባቂ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG