በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሙሴቬኒ ለስድስተኛ ዘመን?


የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ

የዩጋንዳ እንደራሴዎችና የፓርላማው ፖሊስ ትናንት ግብ ግብ ገጥመዋል። ምክንያቱ እንደራሴዎቹ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት የዕድሜ ጣሪያ ገደብ ጉዳይ አንስተው እየተወያዩ ሣሉ ወታደሮች በፓርላማው ግቢ ውስጥ ታዩ መባሉ ነበር። “በዚያው የቃላቱ መሠናዘር ተቋርጦ የአካል ትንቅንቁ ተጀመረ” ብላለች የካምፓላ ሪፖርተራችን ሃሊማ አቱማኒ።

በዩጋንዳ ሕግ መሠረት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለመወዳደር የሚሻ ዕድሜው ከሰባ አምስት መብለጥ የለበትም።

ሰሞኑን የሃገሪቱ ፓርላማ ያንን የዕድሜ ጣሪያ ከፍ ለማድረግ ወይም ለመሠረዝ እየመከረ የመሆኑ ዜና ምናልባት ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ለስድስተኛ የሥልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆኑ እየተሰማ ነው።

የተቃውሞው ጎራ እንደራሴዎችና ከገዥው ፓርቲም የተወሰኑቱ ይህንን አዲስ የሕግ ሃሣብ በብርቱ እየተቃወሙ ናቸው።

ከትናንት በስተያና ትናንት ቁርቁስ ውስጥ የቆየው ፓርላማ ትናንት ከሰዓት በኋላ ወደመደበኛ ሥራው ተመልሶ በሃሣቡ ላይ ግራ ቀኙን እያደመጠ ነው።

በዚያ ላይ የፕሬዚዳንት አንድ የሥልጣን ዘመንን እንዲሁም የእንደራሴዎቹን የሥራ ጊዜ ከአምስት ዓመት ወደ ሰባት ዓመት ከፍ ሊያደርግ በሚችልም ሃራብ ላይ የሕዝብ ተወካዮቹ እየመከሩ ናቸው።

ሁለቱም ሃሣቦች ለድምፅ መቼ እንደሚቀርቡ አልታወቀም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሙሴቬኒ ለስድስተኛ ዘመን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG