በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ተማሪዎች ሞተዋል


ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (Haramaya University)
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (Haramaya University)

በትናንቱ ዕለት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸው ያለፈና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች እንደነበሩ ተገለጸ። በተለይም በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በደረሰ ግጭት የመንግሥት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ተማሮች መሞታቸው ታውቋል።

ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ተማሪ ለኦሮሚኛ ክፍል ባልደረባችን ቱጁቤ ኩሳ በሰጠው ቃል፣ ባለፈው ቅዳሜ የግቢው መብራት ጠፍቶ ውሎ ጠፍቶ እንዳደረ፣ ተማሪውም ይንጫጫና "ፌዴራል ገባ እያለ" ይጮህ እንደነበር አመልክቶ፣ ትናንት ሰኞ ለሰልፍ እንደወጣ አመልክቷል። ይዞ የተነሳውም ጥያቄ መንግሥት ያወጣውን ማስተር ፕላን (Master Plan) የሚቃወም ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቱጁቤ የመንግሥትን ምላሽ ለማግኘት ባደረገችው ጥረት፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ጽቤት በምክትል ኰሚሽነር ማይርግ ቃል-አቀባዩን ሰሎሞን ታደሰን አነጋናግራ የተወሰኑ ኃይሎች ሁከት ፈጥረው የትምህርት ሂደቱ እንዲደናቀፍ ማድረጋቸውን አመልክተው በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለ፥ እንዳውም 12 ፖሊሶች በድንጋይ መደብደባተውን ገልጸዋል።

ቱጁቤ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (Haramaya University) ተማሪው ያነሳቻቸውንና ያገኘችውን መልስ እንድትሰሙ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል እንጋብዛለን።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ሁለት ተማሪዎች ሞተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

XS
SM
MD
LG