በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ለሪፐብሊካን ለዴሞክራትና ገለልተኛ መራጮች አብሮነታችንን የምናጠናክርበት ሠዓት ነው" ዶናልድ ትራምፕ


ዶናልድ ትራምፕ

ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በሰፊው እንደሚያሸንፉ የተተነበየላቸውን የዲሞክራቲክ ፓርቲውን ተቀናቃኛቸውን ሂላሪ ክሊንተንን በአስገራሚ ሁኔታ አሸንፈው 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ተመርጠዋል።

ተዋናዩና ከበርቴ ነጋዴው ትራምፕ ለሊቱን በማንሃትን ሆቴል አዳራሽ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው የድል ንግግር ያሰሙት በከፍተኛ የደስታ ስሜት ነው።

ዶናልድ ትራምፕ በድል ንግግራቸው ወቅት ከቤተሠቦቻቸው ጋር
ዶናልድ ትራምፕ በድል ንግግራቸው ወቅት ከቤተሠቦቻቸው ጋር

የኒውዮርክ ነጋዴ በምርጫው ዘመቻው ወቅት በሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች ተቀድመው ነበር የታዩት ሆኖም በትናንቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማጠቃልያ ምሽት ግን በአስደናቂ ሁኔታ በድል አድራጊነት ብቅ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ሆነዋል፡፡

በዋይትሃውስ ቤተመንግሥት የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሜሪ አልያስ ሳሊናስ በሥፍራው ነበረች፤ ያደረሰችንን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00

አስተያየቶችን ይዩ (2)

XS
SM
MD
LG