በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንደራሴዎች ትረምፕ ስለዓለምም እንዲያስቡ ይፈልጋሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ምሽት ላይ ለተወካዮች ምክር ቤቱ በሚያደርጉት ንግግር ላይ ሃገሪቱ ለረዥም ጊዜ ይዛው በቆየችው ዓለምአቀፍ ግዴታዎቿና ቃሎቿ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንደሚፈልጉ የሁለቱም ገዥ ፓርቲዎች አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ምሽት ላይ ለተወካዮች ምክር ቤቱ በሚያደርጉት ንግግር ላይ ሃገሪቱ ለረዥም ጊዜ ይዛው በቆየችው ዓለምአቀፍ ግዴታዎቿና ቃሎቿ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንደሚፈልጉ የሁለቱም ገዥ ፓርቲዎች አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ተናግረዋል፡፡

በርግጥ ፕሬዚዳንቱ ለተወካዮች ምክር ቤቱ የጋራ ጉባዔ ዛሬ ምሽት ላይ ያደርጉታል የተባለው ንግግር በአመዛኙ የሚያተኩረው በሃገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን የታወቀ ቢሆንም እንደራሴዎቹ ግን ተጨማሪ ፍላጎት አላቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የአሜሪካ አቋምና ቦታ …

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለጤና ጥበቃ ዋስትና ማሻሻያው ትልም ይነድፋሉ ብለው እንደሚያስቡ የተናገሩት ሪፐብሊካኑ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ጃን ትዩን ዓለምአቀፍ ጉዳዮችም ትኩረት እንደሚሹ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ገልፀዋል፡፡

“አትላንቲክ አቋራጭ ለሆኑ ትብብሮቻችን በተለይ ደግሞ ጦር ትብብር ድርጅቱ ኔቶ ያለንን የቁርጠኝነት አቋም ካረጋገጡ ለአውሮፓዊያን አጋሮቻችንና በዓለም ዙሪያ ላሉ ጦሮቻችንም ታላቅ ዜና ይሆናል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል እንደራሴው፡፡

በዚህ የሴናተር ትዩን ሃሣብ ዴሞክራቱ አቻቸው ክሪስ ቫን ሆለንም ይስማማሉ፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም ለሰብዓዊ መብቶች መጠበቅ እንደምትቆም፤ ወዳጆቻችንን እንደምንደግፍ፤ ከሩሲያ ጋር የምንመሣጠር አለመሆናችንን ግልፅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ በጀት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ የሚጠይቅ በጀት አቅርበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

እንደራሴዎች ትረምፕ ስለዓለምም እንዲያስቡ ይፈልጋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG