ለኮቭድ-19 በመጋለጣቸው ለህመም የተዳረጉት የፕሬዚዳንት ትራምፕ የጤንነት ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የጤንነታቸው ሁኔታስ በመጪው የህዳሩ ምርጫ ምን ሊፈጥር እንደሚችል ብዙ ያልታወቁ ነገሮች መኖራቸውም እየተነገረ ነው፡፡ በጆን ሀፕኪንስ ሪፖርት መሰረት እስካሁን በመላው ዓለም 35ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋልጠዋል፡፡ ባላፈው ቅዳሜ ካሉበት ሆስፒታል ሆነው የቪዲዮ መልዕክት የሰደዱት ፕሬዚዳንት ትረምፕን ራሳቸውን በቫይረሱ የተጠቁ ሌሎች ሰዎችን ለመርዳት እንደተሰማራ ሰው አድርገው አያይዘው ተናግረዋል፡፡
ይሄ የደረሰ አጋጣሚ ነው፡፡ በዓለም ላይ ባሉ ሚሊዮን ሰዎች ላይ የደረስ ነገር ነው፡፡ እኔም ለነሱ እየታገልኩ ነው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ አይደለም፣ በዓለም ላይ ላሉት ሁሉ እየታገልግኩላቸው ነው፡፡ ይሄን ኮሮናቫይረስ ወይም እንደፈለጋችሁ አድርጋችሁ ጥሩት ብቻ እናሸንፈዋለን፡፡ በደንብ አድርገን እናሸንፈዋለን!!
ባለፈው እሁድ የፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ስቴሮይድ ዴክሳምታሶን የተባለውን መድሃኒት የሰጧቸው ሲሆን ምናልባትም ዛሬ ሰኞ ወደ ዋይት ሐውስ እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ የጤንነት ችግር የመጣው እሳቸውና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ም/ፕሬዘዳንት ወደ መጨረሻዎቹ 4ቱ የምርጫ ዘመቻዎቻቸው ሳምንታት ምዕራፍ ላይ እንዳሉ ነው፡፡ ትረምፕ ለኮሮናቫይረስ ተጋልጠው ሆስፒታል በመግባታቸው ጆ ባይደን ከምርጫ ዘመቻ ማስታወቂያዎቻቸው ላይ ትረምፕን የሚያጥላሉ ማስታወቂያዎችን ለጊዜው ማቆማቸውን ገልጸዋል፡፡
በም/ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እና በጆባይደን አጋር በሴኔተር ከማላ ኸሪስ መካከል ከነገ በስቲያ ረቡ እ ይካሄዳል የተባለው የምርጫ ክርክር ግን አሁንም እንዳለ ነው፡፡ ጥያቄው ቀሪውን የምርጫ ሳምንታት የፕሬዚዳናት የጤንነት ሁኔት እንዴት አድርጎ ይቀጥላል የሚለው ነው፡፡ የትረምፕ መታመም ግን ለባይደን የምርጫ ዘመቻ ሁለት አቅጣጫዎችን እንዲከተሉ አስገድዷቸዋል፡፡ አንደኛ በትረምፕ መታተመም የተሰማቸውን አዘኔታ እንዲገልጹ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሁለቱ መሪዎች የተሻለ አመራር ሊሰጡ እንደሚችሉ ማሳየት ነው፡፡ የጆ ባይደን የምረጡኝ ዘመቻ ምትክል ሥራ አስኪያጅ ኬት ቤድንግፊልድ እንዲህ ይላሉ
ይሄ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም፡፡ ይሄ ጥያቄ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትን በተቻለው ፍጥነት ወደ ሙሉ ጤንነት የመመለስ ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ በፊት እንደተናገርኩት ስለ ጆ ባይደን የአመራር ዘይቤ አስፈላጊነት መናገራችንን እንቀጥላለን፡፡ ጆ ባይደን ስላላቸው የተካበተ ልምድ፣ አገሪቱን ወደ አንድነት ስለማምጣት ብቃታቸው፣ የጋራ ስምምነት ፈጥሮ ነገሮችን ወደፊት ማንቀሳቀስ ስለመቻል ችሎታቸው የምርጫ ዘመቻች የሚያተኩርበት ይሆናል፡፡
ጄሰን ሚለር የትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በርካታ ጥንቃቄዎችን የወሰዱ ሲሆን ቫይረሱንም እየተፋለሙ አመራር መስጠት የሚችሉ መሆናቸውን አሳይተዋል በማለት እንዲህ ይላሉ
ልክ በጆ ባይደን እናዳየነው እድሜ ልካችንን ዝምብለን ከቤታችን ምድር ቤት አንቀምጠም፡፡ ወደ ውጭ ወጥተን ያለውን ሁኔታ እየተጋፈጥን ህይወታችንን እየኖርን ይህን ነገር አንድ ነገር ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ክትባቱን ወይም ህክምናውን አግኝተን ይህን ቫይረስ ድል መንሳት አለብን፡፡
ለትረምፕ ምናልባት ይህ አጋጣሚ ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ላልወሰኑ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ፡፡ እነዚህ መራጮች በሚቀጥለው ምርጫ ወሳኝ ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉት፣ የሪፐብሊካን ስትራቴጂስት አሊስ ስትዋርት እንዲህ ይላሉ
ማንን እንደሚመርጡ ያልወሰኑትን ማሳመን ይኖርባቸዋል፡፡ የወረርሽኝነቱንም አደገኝነት በሚገባ መንገዘብ በአዘኔታና በሚራራ ልብ ስሜትን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ የወረርሽኙ ሁኔታ ማንን መምረጥ እንዳለባቸው በመወላወል ላይ ባሉት ሰዎች ጭንቅላት ውስጥ ገና ረጅም ጊዜ ይቆያል፡፡
በእርገጠኝነት የሚታወቅ አንድ ነገር ቢኖር ግን፣ ዋይት ሐውስን ለመያዝ፣ ከወዲሁ እጅግ የተካረረ ውጥረት በተሞለበት ሁኔታ ውስጥ፣ መጭው ምን ሊሆን እንደሚችል በ እርገጥኝነት መገመት የማይቻል መሆኑ ነው፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።