በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ መቐለ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ መቐለ ከተማ

በትግራይ ክልል ሰሓርቲ በተባለች ወረዳ የአንድ ቀበሌ አስተዳዳሪ ማኅተም በኃይል ነጥቀዋል የተባሉ የፀጥታ አባላት ወሰዱት በተባለ ርምጃ 17 ሰዎች መጎዳታቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናገሩ።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፣ የሰራዊቱ አባላት ጣልቃ መግባታቸውን ገለፆ፣ “እንዲኽ ያለ ጣልቃ ገብነት ክልሉን ወደ ከባድ ቀውስ ያስገባዋል” ብሏል።

በትግራይ በጸጥታ ኃይሎች እና ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች መጎዳታቸውን ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በወረዳ አስተዳዳሪነት የተሾሙት፣ አቶ አታኽልቲ ግርማይ ለአሜሪካ ድምፅ “የፀጥታ አባላት ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወግነው ወደ ሕዝብ መተኮስ ሳይኾን፣ የሥራ ድርሻቸው ሰላም እና ፀጥታ መጠበቅ ነው”ብለዋል።

በድርጊት ፈጻሚነት የተወቀሰውና፣ “አርሚ 26” ተብሎ የሚጠራው የክልሉ የፀጥታ መዋቅር አዛዥ ኮሌኔል ሓጎስ ገብረ፣ የፀጥታ አባላቱ ወደ አከባቢው የገቡት በሕዝብ ጥሪ መኾኑን ገልፀው “በነዋሪዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ የለም” ብለዋል። “ክሱ የሰራዊታችን ስም ማጥፋት ነው” ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG