በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነቱ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ተገለፀ


የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ካምፖች ላይ ጥቃት እንደፈፀመ የሚገልፁ ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሰቧቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ገለጹ።

የራሱን ሠራዊት የሚከብ የክልል መንግሥት፣ በዓለም ታይቶ አይታወቅም ያሉት የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ህወሓትን በክህደት ወንጅሏል።

ሠራዊቱ የህወሓትን ከበባ በከፍተኛ ጀግንነት መመከቱን እና እየመከተም መሆኑን የገለፁት ጄነራል ብርሃኑ በከበባ እጅ እንዲሰጥና ወደ እነሱ እንዲገባ ያደረጉት ጥረትም አልተሳካም ብለዋል።

መከላከያ ሃይሉ ህዝብ እንዳይጎዳ ፅንፈኛ ሃይሉን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ ነው በማለትም አብራርተዋል።

በተያያዘ ዜና ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ካምፖች ላይ ጥቃት እንደፈፀመ የሚገልፁ ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሰቧቸው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

በጦርነቱ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00


XS
SM
MD
LG